ሠንደቅ ዓላማ እና ሠራዊት ከቃል እስከ ህይወት መስዋዕትነት የተገመደ ትስስር አላቸው       ጀኔራል ጌታቸው ጉዲና

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ጥቅምት 03 ቀን 2018 ዓ.ም

“ሠንደቅ ዓላማችን ለኢትዮጵያ ታላቅ የከፍታ ዘመን ብሥራት፣ ለብሔራዊ አንድነታችን፣ ለሉዓላዊነታችንና ለኢትዮጵያ ሕዳሴ” በሚል መሪ ሃሳብ ብሄራዊ የሠንደቅ ዓላማ ቀን በመከላከያ ሚኒስቴር ጠቅላይ መምሪያ ተከብሯል።

በዕለቱ በክብር እንግድነት የተገኙት ጀኔራል ጌታቸው ጉዲና የብሔራዊ ሰንደቅ ዓላማ ከፍታ  ከሀገራዊ ክብርና ማንነት ጋር በቀጥታ የተቆራኘ በመሆኑ የሀገር ክብር የሚረጋገጠው ደግሞ ብሔራዊ ጥቅሞቻችን በተሟላ መንገድ ሲጠበቅ ነው ብለዋል።

ታሪካዊ ጠላቶቻችን በቻሉት ሁሉ የሀገራችንን ብሔራዊ ጥቅም በመፃረር በእጅ አዙር የውስጥ ባንዳዎችን በማደራጀት እና በመደገፍ ሲውተረተሩ ይስተዋላሉ ያሉት ጀኔራል መኮንኑ ተላላኪ ባንዳዎችም የተሰጣቸውን አጀንዳና እኩይ አላማ ለማስፈፀም ከዚህም ከዚያም በትጥቅ እንቅስቃሴ ቢያደርጉም ከንቱ ምኞታቸው መክኗል ሲሉ ገልፀዋል።

ጄኔራል ጌታቸው ጉዲና ሀገራችን ኢትዮጵያም በዚህ ትውልድ ዘመን ከህዝቦቿ እና ከሠራዊቷ ጋር ሆና ወደ ከፍታ ዘመን ትሸጋገራለች ነው ያሉት።

ሠንደቅ ዓላማ እና ሠራዊታችን ከቃል እስከ ህይወት መስዋዕትነት የተገመደ ትስስር አላቸው ያሉት ጀኔራል ጌታቸው ጉዲና የሀገራችን መንግስትና ህዝብ ያነገቡትን ሀገራዊ ጥቅም የማረጋገጥ አጀንዳ እውን ለማድረግ እኛ የሠራዊት አመራሮችና አባላት የተጣለብንን ሀላፊነት በላቀ ደረጃ በመፈፀም በሠንደቅ ዓላማችን ስር የገባነውን ቃል በተግባር ላይ ልናውል ይገባልም ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል።

ወቅታዊ አጀንዳ

mf
ኢትዮጵያ የዓለም አቀፍ የንግድ መስመሮች አካል መሆን እንዳለባት የፈረንሣይ የምድር ኃይል አዛዥ ጄነራል ፒየር ሺል ገለፁ።
ay3
የመከላከያ ሚኒስትር ኢንጂነር አይሻ መሃመድ ከኳታር ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የመከላከያ ሚኒስትር ጋር ተወያዩ።
Y
ፈረንሣይ ከኢትዮጵያ ጋር በወታደራዊ መስክ የበለጠ ለመሥራት ዝግጁ መሆኗን የፈረንሣይ ምድር ጦር አዛዥ ጄኔራል ፒየር ሺል ገለፁ።
F
ኢትዮጵያ ከአሜሪካ ጋር ያላት ወታደራዊ ግንኙነት ተጠናክሮ ይቀጥላል፦   ክቡር ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ
A1
አንድ ሆነን በአድዋ እንዳስመዘገበነው ድል በጋራ ሆነን የአክሲዮን ማህበራችንን ስኬት እናረጋግጥ፦    ክብርት ኢንጂነር አይሻ መሃመድ
P
በሶማሊያ ሴክተር 3 የብሄራዊ ድጋፍ ሰጪ ቡድን አባላት የ18 ወራት ተልዕኳቸውን አጠናቀው ተመለሱ፡፡

ስፖርት

ኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት

ለህገ መንግስቱ፣ ለሀገራችን መንግስትና ህዝቦች ፍፁም ታማኝ የሆነ፣ ጦርነትን የሚያቆም የልህቀትና የፍቅር ማዕከል የሆነ፣ በአስተማማኝ እና በብቃት በአገር አቀፍና በአለም አቀፍ ግዳጅ የሚያሳካ ዘመናዊ የመከላከያ ሰራዊት ማየት።

ማህበራዊ ሚዲያ