ሠራዊቱ በከፈለው መስዋዕትነት የቀጠናው ሠላም ተረጋግጧል።    ርዕሰ መስተዳድር አቶ አሻደሊ ሀሰን

የቤኒ ሻንጉል ጉምዝ ህዝቦች ክልል አሁናዊ የፀጥታ ሁኔታ በተመለከተ ከምዕራብ ዕዝ ኮማንድና ከፍተኛ መኮንኖች እንዲሁም ከክልሉ ባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት ተካሂዷል።

በዚህ ወቅት ሠራዊቱ መስዋዕትነት በመክፈል የክልሉንና ሀገራዊ ሠላምን እያረጋገጠ መሆኑን የቤኒሻንጉል ጉምዝ ህዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አሻደሊ ሀሰን ተናግረዋል።

ክልሉ የተለያዩ ፀረ-ሠላም ሀይሎችና ሰርጎ ገቦች እንቅስቃሴ የሚስተዋልበት አካባቢ ቢሆንም በሰራዊቱ የጀግንነት ተጋድሎ ሴራቸው እየመከነ መሆኑን የገለፁት አቶ አሻደሊ ሀሰን፤ ዘላቂ ሠላምን ለማረጋገጥ ሠራዊቱ በሚያደርገው ሁለንተናዊ ጥረት የክልሉ መንግስትና ህዝብ የበኩሉን ሚና ለመጫወት ሁሌም ቁርጠኛ መሆኑን አረጋግጠዋል።

በውይይት መድረኩ ላይ የተገኙት የምዕራብ ዕዝ ዋና አዛዥ ሜጄር ጀኔራል አማረ ባህታ በበኩላቸው፤ ምዕራብ ዕዝ በተሰማራባቸው የግዳጅ ቀጠናዎች ሁሉ አሸባሪውን ሸኔንና ፅንፈኛውን ፋኖ እንዲሁም ሌሎች ፀረ-ሠላም ሀይሎችን የመደምሰስ ተልዕኮውን በተሳካ ሁኔታ እየፈፀመ መሆኑን ገልፀዋል።

ዓላማችንና ግባችን ኢትዮጵያን ማፅናት ነው። በመሆኑም ከዚህ ቀደም በግዳጅ ቀጠናችን ከሚገኙ ከአካባቢው መስተዳድር አካላት፣ ሌሎች የፀጥታ ኃይሎችና የአካባቢው ህብረተሰብ ጋር በመቀናጀት ያስመዘገብናቸውን ድሎች በማጎልበት ለህዝባችን ሠላምና ልማት ምቹ ሁኔታ የመፍጠር ተልዕኳችን ለመወጣት ቀን ከሌት እንሰራለን ብለዋል።

አዛዡ የኢትዮጵያን ልዕልናና የህዝቦቿን ሠላም ለማናጋት ሴራ ሲጎነጉኑ ውለው የሚያድሩ የጥፋት ኃይሎች የፈለጉትን ያክል ቢፍጨረጨሩም ከመላው ህዝባችን ጋር ሆነን  ፈተናዎችን ተሻግረን ድል እናሥመዘግባለን ነው ያሉት።

የምዕራብ ዕዝ እና የክልል ባለድርሻ አካላት ቀጣይ የፀጥታ የስራ አቅጣጫዎችንም አስቀምጠዋል።
ዘገባው የምዕራብ ዕዝ የሠራዊት ስነ-ልቦና ግንባታ ነው

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official

ወቅታዊ አጀንዳ

mf
ኢትዮጵያ የዓለም አቀፍ የንግድ መስመሮች አካል መሆን እንዳለባት የፈረንሣይ የምድር ኃይል አዛዥ ጄነራል ፒየር ሺል ገለፁ።
ay3
የመከላከያ ሚኒስትር ኢንጂነር አይሻ መሃመድ ከኳታር ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የመከላከያ ሚኒስትር ጋር ተወያዩ።
Y
ፈረንሣይ ከኢትዮጵያ ጋር በወታደራዊ መስክ የበለጠ ለመሥራት ዝግጁ መሆኗን የፈረንሣይ ምድር ጦር አዛዥ ጄኔራል ፒየር ሺል ገለፁ።
F
ኢትዮጵያ ከአሜሪካ ጋር ያላት ወታደራዊ ግንኙነት ተጠናክሮ ይቀጥላል፦   ክቡር ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ
A1
አንድ ሆነን በአድዋ እንዳስመዘገበነው ድል በጋራ ሆነን የአክሲዮን ማህበራችንን ስኬት እናረጋግጥ፦    ክብርት ኢንጂነር አይሻ መሃመድ
P
በሶማሊያ ሴክተር 3 የብሄራዊ ድጋፍ ሰጪ ቡድን አባላት የ18 ወራት ተልዕኳቸውን አጠናቀው ተመለሱ፡፡

ስፖርት

ኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት

ለህገ መንግስቱ፣ ለሀገራችን መንግስትና ህዝቦች ፍፁም ታማኝ የሆነ፣ ጦርነትን የሚያቆም የልህቀትና የፍቅር ማዕከል የሆነ፣ በአስተማማኝ እና በብቃት በአገር አቀፍና በአለም አቀፍ ግዳጅ የሚያሳካ ዘመናዊ የመከላከያ ሰራዊት ማየት።

ማህበራዊ ሚዲያ