ዕዙ ማንኛውንም ተልዕኮ መፈፀም በሚያስችለው የዝግጁነት ደረጃ ላይ ይገኛል።     ሌተናል ጄኔራል ብርሃኑ በቀለ

ዕዙ ከየትኛውም አቅጣጫ ሊሰነዘር የሚችል ጥቃትን መመከት በሚያስችለው የዝግጁነት ደረጃ ላይ ይገኛል ሲሉ የሰሜን ምዕራብ ዕዝ ዋና አዛዥ ሌተናል ጄኔራል ብርሃኑ በቀለ ተናገሩ ።

ዋና አዛዡ ከዕዙ ከፍተኛ አመራሮች ጋር በዕዙ የግዳጅ  ቀጣናዎች አሁናዊ የተልዕኮ አፈፃፀም ዙሪያ የመስክ ምልከታና  ቅኝት አድርገዋል።

ሌተናል ጄኔራል ብርሃኑ በቀለ ከከፍተኛ አመራሮቹ ጋር በነበራቸው ቆይታ የሠራዊቱ ዝግጁነትና ተልዕኮ አፈፃፀም የባዳውን ዕኩይ ሴራዎች መከታተልና መቆጣጠር በሚያስችል ደረጃ የተጠናከረ መሆኑን አንሰተዋል።

የባንዳዎቹ ተስፋ ከባዳዎቹ ነው ያሉት ሌተናል ጄኔራል ብርሃኑ በቀለ ባንዳዎቹ ህይወታቸውን ለማቆየት ከባዳዎቹ የሚጠብቁት ፍርፋሪና ባዳዎቹ በህገወጥ መንገድ ማግበስበስ የሚፈልጉት የኢትዮጵያ አንጡራ ሃብት በጠንከራ ቁጥጥርና ክትትል የበለጠ መጥበብ አለበት ሲሉም አሳስበዋል።

የሠራዊቱ አሰፋፈር፣ ቁርጠኝነትና የስነ-ልቦና ዝግጁነት ከመቼውም ጊዜ የላቀ ነው ያሉት ዋና አዛዡ ሌተናል ጄኔራል ብርሃኑ በቀለ ባዳዎቹ ስለ ኢትዮጵያ ምንም ሊያስቡ ይችላሉ ነገር ግን ለመተንኮስ ሲያስቡ ከባድ ዋጋ እንደሚከፍሉም ጭምር ማሰብ ይገባቸዋልም ብለዋል።

በፅንፈኛው ላይ እየተወሰደ ባለው እርምጃ በላኪውም ሆነ በተላላኪው ላይ ድንጋጤ ፈጥሯል ያሉት አዛዡ ሌተናል ጄኔራል ብርሃኑ በቀለ የሠላም አማራጭ በማይከተሉ፣የኢትዮጵያን ልማት በሚያደናቅፉና የባዳዎቹን ተልዕኮ ለማስፈፀም በሚፍጨረጨሩ ኃይሎች ላይ የምንወስደው እርምጃ ጠንከር ያለ ነው ሲሉ አፅንኦት ሰጥተው ተናግረዋል።
ዘገባው የሰሜን ምዕራብ ዕዝ ሚዲያና ህዝብ ግንኙነት ነው።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official

ወቅታዊ አጀንዳ

mf
ኢትዮጵያ የዓለም አቀፍ የንግድ መስመሮች አካል መሆን እንዳለባት የፈረንሣይ የምድር ኃይል አዛዥ ጄነራል ፒየር ሺል ገለፁ።
ay3
የመከላከያ ሚኒስትር ኢንጂነር አይሻ መሃመድ ከኳታር ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የመከላከያ ሚኒስትር ጋር ተወያዩ።
Y
ፈረንሣይ ከኢትዮጵያ ጋር በወታደራዊ መስክ የበለጠ ለመሥራት ዝግጁ መሆኗን የፈረንሣይ ምድር ጦር አዛዥ ጄኔራል ፒየር ሺል ገለፁ።
F
ኢትዮጵያ ከአሜሪካ ጋር ያላት ወታደራዊ ግንኙነት ተጠናክሮ ይቀጥላል፦   ክቡር ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ
A1
አንድ ሆነን በአድዋ እንዳስመዘገበነው ድል በጋራ ሆነን የአክሲዮን ማህበራችንን ስኬት እናረጋግጥ፦    ክብርት ኢንጂነር አይሻ መሃመድ
P
በሶማሊያ ሴክተር 3 የብሄራዊ ድጋፍ ሰጪ ቡድን አባላት የ18 ወራት ተልዕኳቸውን አጠናቀው ተመለሱ፡፡

ስፖርት

ኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት

ለህገ መንግስቱ፣ ለሀገራችን መንግስትና ህዝቦች ፍፁም ታማኝ የሆነ፣ ጦርነትን የሚያቆም የልህቀትና የፍቅር ማዕከል የሆነ፣ በአስተማማኝ እና በብቃት በአገር አቀፍና በአለም አቀፍ ግዳጅ የሚያሳካ ዘመናዊ የመከላከያ ሰራዊት ማየት።

ማህበራዊ ሚዲያ