የመከላከያ ሚኒስትር ኢንጂነር አይሻ መሀመድና የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር መቅደስ ዳባ በቢሸፍቱ የመከላከያ ስፔሻላይዝድ ሪፈራል ሆስፒታል በመገኘት የንፅህና አስተዳደር ስርዓቱን ስታንዳርድ ለመጠበቅ እየተከናወኑ ያሉ ተግባራትን ጎብኝተዋል፡፡
ሚኒስትሮቹ የሆስፒታሉን የንፅህና ስርዓት አቅም ለማዘመንና ለማስፋት እየተሰሩ ያሉ ስራዎችን ተዘዋውረው የጎበኙ ሲሆን በአንድ አገር ወዳድ ኢትዮጵያዊ የሆስፒታሉን የላውንደሪና የሃይጂን ስርዓቱን በማዘመን ተግባራዊ ስልጠና በመስጠት ስራውን ለማሳለጥ የተደረገውን ጥረትም ተመልክተዋል፡፡

ይህ ጥረት የሆስፒታሉን አጠቃላይ የመገልገያ አልባሳት፣ የታካሚ ልብሶችንና ቁሳቁሶችን እንዲሁም ሙሉ የንፅህ አጠባበቅ ሂደቱን ዘመናዊና ከዓለም አቀፍ ስታንዳርድ ጋር በማጣጣም የደህንነት መስፈርቶችን እንዲያሟላ ለማድረግ የሚያግዝ መሆኑም ተመልክቷል፡፡
ፖሽ የላውንደሪና የሃይጂን ሶሉሽን በተሰኘው ድርጅት ድጋፍ የተከናወነው ይህ ዘመናዊ የንፅህና ስርዓት አተገባበር ሆስፒታሉ ደህንነቱ በተጠበቀ መልኩ አገልግሎት እንዲሰጥና የኢንፌክሽን መከላከል አቅሙን ይበልጥ የሚያሻሽል መሆኑም የተገለፀ ሲሆን ድርጅቱ ለሆስፒታል ባለሙያዎች ተከታታይና ተግባራዊ ስልጠና በመስጠት ሂደቱ የተሳካ እንዲሆን ከማድረጉም በላይ የሰራተኞች የፅዳት ዩኒፎርሞችን፣ደረጃቸውን የጠበቁ የላውንደሪ ኬሚካሎችንና አንሶላዎች ድጋፍ ማድረጉም ተመልክቷል፡፡
ሚኒስትሮቹ የድርጅቱ ባለቤት አቶ መሃመድ ቡሽራ ለሆስፒታሉ ያበረከቱት ድጋፍ የሚደነቅ መሆኑን በመግለፅ ዕውቅናና ምስጋና ሰጥተዋቸዋል፡፡

የመከላከያ ስፔሻላይዝድ ሪፈራል ሆስፒታል በኢትዮጵያ ውስጥ ልዩ የህክምና አገልግሎቶችን በመስጠት ረገድ ወሳኝ ሚና እየተጫወተ የሚገኝ ሲሆን አሁን የተዘረጋው ዘመናዊ የንፅህና አጠባበቅ ስርዓት የታካሚዎችን ደህንነት ይበልጥ በማሻሻል ከሀገር ውጭ የሚደረግ የህክምና ጉዞን በመቀነስ አስተዋፅኦ እንደሚያደርግ ይጠበቃል። በጉብኝቱ ላይ ጄኔራል መኮንኖች፣ ከፍተኛ የህክምና ባለሙያዎችና የሆስፒታሉ ሰራተኞች ተገኝተዋል፡፡ ዘገባውን ያደረሠን የሚኒስቴሩ ፅህፈት ቤት ነው
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ቴሌግራም
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official





