ለሶስት ቀናት የስራ ጉብኝት በኳታር ዶሃ የሚገኙት የኢፌዴሪ መከላከያ ሚኒስቴር ሚኒስትር ክብርት ኢንጂነር አይሻ መሀመድ በዛሬው ዕለት የኳታር ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የመከላከያ ሚኒስቴር ሚኒስትር ከሆኑት ሼክ ሳኡድ ቢን አብዱራህማን ቢን ሀሰን አል ታኒ ጋር በሁለትዮሽ ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል፡፡

በውይይታቸውም በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ይበልጥ ለማጠናከርና ለጋራ ጥቅም ትብብሮችን ለማሳደግ ፍላጎት እንዳላቸው ተናግረዋል፡፡
በተለይም በመከላከያ ልዩ ልዩ ዘርፎች ያላቸውን ትብብር ለማሳደግና ለማጠናከር በሚቻልባቸው መንገዶች ላይ ባደረጉት ውይይት በተለያዩ ኢንቨስትመንትና የአቅም ግንባታ መስኮችም ትብብራቸውን ለማሳደግ ፅኑ ፍላጎት እንዳላቸው አመላክተዋል፡፡ ዘገባውን ያደረሰን የሚኒስቴሩ ፅህፈት ቤት ነው።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ቴሌግራም
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official





