FDRE Defense Force - የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት
36.3K subscribers
25K photos
19 videos
9 files
6.85K links
# ቁልፍ እሴቶች
1, ከራስ በፊት ለህዝብና ለሀገር ጥቅም፣
2, ምንጊዜም የተሟላ ስብዕና፣
3, ያልተሸራረፈ ዲሞክራሲያዊ አስተሳሰብ፣
4, በማንኛውም ግዳጅ ወይም ተግባር የላቀ ውጤት።
Download Telegram
የተሳካ የግዳጅ አፈፃፀም በመኖሩ የአካባቢውን ሰላም ማረጋግጥ ተችሏል።
      ሌተናል ጀኔራል መሰለ መሰረት

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ጥር 25 ቀን 2017 ዓ.ም

የምዕራብ ዕዝ ዋና አዛዥ ሌተናል ጀኔራል መሰለ መሰረት የዋልታ ኮር የግዳጅ አፈፃፀምን በተመለከተ ከሠራዊቱ ጋር ውይይት አድርገዋል።

በምስራቅ ወለጋ ዞን ጊዳ አያና ወረዳ ተገኝተው ከሰራዊቱ ጋር  ውይይት ያካሄዱት ሌተናል ጀኔራል መሰለ መሰረት የዕዙ ሠራዊት ቀን ከሌሊት በሚያደርገው ጠንካራ ስምሪት የአካባቢው ሰላም አስተማማኝ ደረጃ ላይ መድረሱን አውስተው የተጀመረውን ሽብርተኛና ፅንፈኛ ሀይል የማጥፋት ስራዎች ይበልጥ አጠናክረን በመሄድ ውጤት ተኮር ተግባራት መከናወን አለበትም ብለዋል።

ለቀጠናው ሰላምና መረጋጋት የዋልታ ኮር  እያደረገ ያለው ውጤታማ ስምሪት የሚደነቅ ነው ያሉት ጀኔራል መኮንኑ ሰራዊቱ በቁርጠኝነትና በከፍተኛ የዓላማ ፅናት ችግሮችን ተቋቁሞ የተሰጠውን ተልዕኮ በአመርቂ ውጤት በመፈፀሙ የቀጠናው ሰላም አስተማማኝ ደረጃ መድረሱን ጠቁመዋል።

የቀረበለትን የሰላም መንገድ አልቀበልም ብሎ በሀይል ምኞቴን አሳካለሁ በማለት ጫካ የገባው ሽብርተኛም ይሁን ፅንፈኛው ሀይል በጉልበትና ነፍጥን በማንገብ የትም መድረስ እንደማይችል ሠራዊቱ አስተማሪ በሆነ መንገድ እርምጃ ወስዶ ማሳየት መቻሉንም ሌተናል ጀኔራል መሰለ መሰረት አስገንዝበዋል።

የኮሩ ዋና አዛዥ ብርጋዲየር ጀኔራል ሀብታሙ ምህረቴ የኮሩ ሠራዊት ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይል በሚያደርገው ስምሪት በየጊዜው በአሸባሪው የሸኔ ቡድንና በፅንፈኛው ሀይል ላይ የማያዳግም እርምጃ በመውሰዱ ህዝቡ በሰላም ወጥቶ እንዲገባ ትልቅ ሚና መወጣቱን ተናግረዋል።

ዘጋቢ ወንድወሰን ፍቃዱ
ፎቶግራፍ ብርቱካን ሙሳ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https:///channel/UCgcF4HWzgNZRsmMlUlb8ebQ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
የሠላምን መንገድ መምረጥ ህዝብን ለመካስ ዕድል የሚሰጥ የሰለጠነ አስተሳሰብ ማሳያ  ነው።
      ሌተናል ጄኔራል ብርሃኑ በቀለ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ጥር 25 ቀን 2017 ዓ.ም

የመረጣችሁት የሰላም መንገድ በብዙ የምታተርፉበት ነው፤የሠላምን መንገድ መምረጥና መከተል ደግሞ የሰለጠነ አስተሳሰብ ማሳያ ነው ሲሉ የሰሜን ምዕራብ ዕዝ አዛዥ ሌተናል ጄኔራል ብርሃኑ በቀለ ተናገሩ።

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የሠላም አማራጭን ተቀብለው በዳባት የተሃድሶ ማዕከል ስልጠናቸውን ላጠናቀቁ  ሰልጣኞች ንግግር ያደረጉት ሌተናል ጄኔራል ብርሃኑ በቀለ ሀገርና ህዝብን ለማዳን የመረጣችሁት የሰላም መንገድ በብዙ የምታተርፉበት እንዲሁም  ህዝባችሁን የምትክሱበት ዕድልን የሚሰጣችሁ ነው ብለዋል ፡፡

ለኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊያን የሚያስፈልገው ሰላምና ልማት ነው ያሉት ሌተናል ጄኔራል ብርሃኑ በቀለ ፅንፈኛውና ዘፊው ቡድን የአማራ ክልል ህዝብን ሠላም በማሳጣት ለከፋ ችግር ዳርጎት ቆይቷል ነው ያሉት ፡፡

ፅንፈኛው ቡድን የኢትዮጵያን መልማትና ማደግ በማይፈልጉ ታሪካዊ ጠላቶቻችን እየታዘዙ በክልሉ የጤና አገልግሎት መስጫና የትምህርት ተቋማት ላይ ወድመትና ኪሳራን በማድረስ በክልሉ በትምህርት ገበታ መገኘት የሚገባቸው ህፃናት ወደ ትምህርት ገበታቸው እንዳይገኙ እንዲሁም በፌደራልና በክልሉ መንግስት ሊሰሩ የታቀዱ ፕሮጀክቶች እንዳይሰሩ ማድረጉን ሌተናል ጄኔራል ብርሃኑ በቀለ ተናግረዋል።

የሠላምን  አማራጭ ተከትለው እጃቸውን ለሚሰጡ ታጣቂዎች አሁንም ቢሆን  በሩ ክፍት ነው ያሉት የሰሜን ምዕራብ ዕዝ አዛዥ ሌተናል ጄኔራል ብርሃኑ በቀለ ከዚህ ውጪ በሚደረግ እንቅስቃሴ ላይ የሚወሰደው እርምጃ ጠንከር ያለ ነው ሲሉም አሳስበዋል።

ሰልጣኞቹ በበኩላቸው በተሳሳተ የፅንፈኛው ፕሮፖጋንዳ  ተታለን ህዝባችንን በድለናል ለከፋ ችግርም ዳርገናል ስለሆነም  የበደልነውን ህዝብ ይቅርታ እንጠይቃለን ሌሎች ወንድሞቻችንም እጃቸውን ሰጥተው ህዝባቸውን እንዲክሱ መልእክታችንን እናስተላልፋለን ሲሉ  ተናግረዋል፡፡

ዘጋቢ አንዷለም ከፍያለው
ፎቶግራፍ  አንዷለም ከፍያለው

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https:///channel/UCgcF4HWzgNZRsmMlUlb8ebQ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
ክፍለ ጦሩ ከፅንፈኛው ያስለቀቃቸውን የህዝብ ተሸከርካሪዎች ለባለንብረቶች አሥረከበ።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ጥር 25 ቀን 2017 ዓ.ም

በሰሜን ጎጃም ዞን አማሪት፣ ዳና ማርያምና ጎጃው  አካባቢ ፅንፈኛውን ሃይል በመደምሰስ ከህዝብ የዘረፋቸውን ተሸከርካሪዎችና ቀብሯቸው የነበረ ቁምቡላዎችን የምስራቅ ዕዝ ክፍለ ጦር አባላት ባደረጉት የተጠናከረ ስምሪት በቁጥጥር ስር ማዋል ተችሏል።

የክፍለ ጦሩ አዛዥ ኮሎኔል ግፋወሰን አበበ ፅንፈኛው ሃይል የክልሉን ሰላም በማደፍረስ የዘረፋ ዓላማውን ለማሳካት ቢጥርም የክፍለጦሩ ሠራዊት ባደረገው ብርቱ ክትትል ንብረቱን  ማስመለስ ተችሏል ብለዋል።

በስምሪቱም 01 ሰሊጥ የጫነ ከባድ ተሸከርካሪ፣  01 የቻይና የኮንሰትራክሽን አይሱዙ፣ 01 የመንግሰት ላንድ ክሮዘርና 01 ካዚኖ ገልባጭ ከፅንፈኛው ማሥመለስ መቻሉን ተናግረዋል።

አሁን የተገኘውን አንፃራዊ ሰላም የበለጠ ለማጠናከር ፅንፈኛውን የገባበት በመግባት አሳዶ በመምታት ተሸከርካሪዎቹን ለባለ ንብረቶቹ አስረከበናል ብለዋል።

አካባቢው የበለጠ ሰላሙ እንዲጠናከር የአካባቢው ማህበረሰብ፣ ወጣቱና የፀጥታ ሃይሉ ከሠራዊቱ ጎን በመሆን የበኩላቸውን ሚና ሊወጡ እንደሚገባ አሳሰበዋል።

ዘጋቢ አወል መሃመድ
ፎቶግራፍ ክፍለ ጦሩ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https:///channel/UCgcF4HWzgNZRsmMlUlb8ebQ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
በሳምንቱ የተከናወኑ አበይት ርዕሠ ጉዳዮች

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ጥር 25 ቀን 2017 ዓ.ም

የኢፌዴሪ ጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ በመከላከያ መሃንዲስ ዋና መምሪያ እየተገነቡ ያሉ ፕሮጀክቶችን የጎበኙት በተጠናቀቀው ሳምንት ነው።

ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ በመከላከያ መሃንዲስ ዋና መምሪያ የተገነባውን ዘመናዊ የብሎኬት እና የቴራዞ ማምረቻ ፋብሪካን የተመለከቱ ሲሆን ማምረቻ ፋብሪካው የተለያዩ አይነቶች ሃያ ሺህ ብሎኬት በቀን ማምረት የሚችል ከመሆኑም በላይ ክላስ ኤ፣ ክላስ ቢ እና ክላስ ሲ ብሎኬቶችን እንደተጠቃሚው ፍላጎት እንደሚያመርት እና በቅርቡ ሥራ እንደሚጀምር በመሃንዲስ ዋና መምሪያ አመራሮች ተገልጿል።

የባህር ሃይል ጠቅላይ መምሪያ ግንባታና የመሃንዲስ ዋና መምሪያ ፕሮጀክቶችን የጎበኙት የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ከምልከታቸው በመነሳት ለቀጣይ ሥራ ይበልጥ ሊያግዙ የሚችሉ ሃሳብ እና አሥተያዬት ሠጥተዋል።
=============

ባሳለፍነው ሳምንት በመከላከያ ዋር ኮሌጅ "በውስብስብ የብሔራዊ ደህንነት አውድ ወስጥ ስትራቴጂካዊ ትብብር እና ተጠያቂነትን ማጎልበት" የሚል መሪ ቃልን የያዘ ውይይት ተካሂዷል።

የተከበሩ ጋትሉዋክ ቱት በአሁኑ ወቅት በሀገራችን ከውስጥም ሆነ ከውጭ የተደቀኑብንን ብሔራዊ ደህንነት ስጋቶች ለመቋቋም የሲቪል እና የደህንነት ተቋማት መተማመን በሰፈነበት ሁኔታ በትብብርና በቅንጅት መስራት ይገባቸዋል ብለዋል።

የመከላከያ ትምህርትና ስልጠና ዋና መምሪያ ሀላፊ ሌተናል ጄኔራል ይመር መኮነን በሰጡት የማጠቃለያ ሀሳብ የምክክሩ ጉዳይ የመከላከያ ሰራዊቱ ብቻ ሳይሆን የሁሉም የሲቪል፣ የደህንነትና ፀጥታ ኃይል ነው ፤ ቀጣይም ውሳኔ ሰጪ አከላትን ያካተተ ውይይት ያስፈልጋል ነው ያሉት።
===============

በአማራ ክልል የአገሪቱን ሉዓላዊነት አደጋ ላይ በመጣል የህዝቦችን ሰላም በማደፍረስ ስልጣንን እንቆጣጠራለን የሚሉ ፅንፈኞችን በመደምሰስ ህግን የማስከበር ስራ መሠራቱ የተገለፀው በዚሁ ሳምንት ነው ።

የጎጃምና ደቡብ ጎንደር ኮማንድ ፖስት አስተባባሪና የምስራቅ ዕዝ ዋና አዛዥ ሌተናል ጄኔራል መሃመድ ተሰማ በባህር ዳር ዙሪያ አንዳሳና ጭስ አባይ ግዳጅ የሚወጡ የሰራዊት ክፍሎች ጋር ባደረጉት ውይይት ፅንፈኛው ሃይል ህግና ስርዓት ባለበት ሃገር ፍላጎታቸውን በሃይል ለማሳካት ያደረጉትን ህገ-ወጥ ድርጊት መታደግ ተችሏል ብለዋል።

ክልሉን የብጥብጥ አውድማ በማድረግ የሰዉ ህይወት እያጠፋና እየዘረፈ  ያለውን ፅንፈኛ ሃይል በመምታት ዕዙና ሌሎች ክፍሎች በጋራ በመሆን ክልሉን ከመበተን አደጋ ታድገናል ያሉት ሌተናል ጄኔራል መሃመድ ክልሉ መንግስታዊ መዋቅሩን ዘርግቶ ተረጋግቶ እንዲሰራ አድርገናል ሰሉ ተናግረዋል።
=============

የኮማዶና አየር ወለድ ዕዝ አዛዥ ሌተናል ጄኔራል ሹማ አብደታ የልዩ ሀይል ፀረ-ሽብር አባላት ምርቃት ላይ በመገኘት የአየር ወለድ ልዩ ምልክት የሆነውን የደረት ክንፍ ለተመራቂዎች ያለበሱት በተጠናቀቀው ሳምንት ነው።

የአየር ወለድ ስልጠና የወሰዱት የክፍሉ አባላት ቀደም ብለው እጅግ ፈታኝና ውስብስብ የሆነ የልዩ ሀይል ፀረ- ሽብር ስልጠናን መውሰዳቸውን አስታውሰው የክፍሉ አባላት የአየር ወለድ ስልጠናን በተጨማሪነት መሰልጠን አስፈላጊና ወሳኝ በመሆኑ ስልጠና መሰጠቱን ተናግረዋል፡፡

የልዩ ሀይል ፀረ-ሽብር አባላት በግልም ሆነ በቡድን የሚሰጣቸውን ውስብስብና ልዩ ግዳጅ ለመወጣ የሚያስችላቸው አቅም እንዲኖራቸው ተደርገው በላቀ ደረጃ መሰልጠናቸውን ገልፀዋል።
============

የአፋር ክልል ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ አቶ ገዶ ሀምሎ የክልሉ የፀጥታ ኃይል ከኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ጋር ተቀናጅቶ በፈፀማቸው ስኬታማ ተልዕኮዎች የአካባቢው ሰላም ዘላቂነት መረጋገጡና ሁሉን አቀፍ እድገት መመዝገቡ ገልፀዋል።

የአፋር ሰላምና ፀጥታ ቢሮ የክልሉ የፀጥታ ኃይል እና በቀጠናው የሚገኘው የሰሜን ምስራቅ ዕዝ በጥምረት ባከናወኑት የሰላምና ፀጥታ ጥበቃ ስራዎች ክልሉ በአስተማማኝ ሰላም ላይ እንደሚገኝ የቢሮው ኃላፊ አቶ አዶ ሃምሎ ተናግረዋል። 

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https:///channel/UCgcF4HWzgNZRsmMlUlb8ebQ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official