አሰራርን ለማዘመን የሚደረጉ የጋራ ጥረቶች ለዘመናዊ ተቋም ግንባታ ጉልህ ሚና እንዳላቸው ተገለፀ።
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት መስከረም 11 ቀን 2019 ዓ.ም
የማዕከላዊ ዕዝ ጤና መምሪያ ከዕዙ አይሲቲ ዲፓርትመንት ጋር በመቀናጀት እንደ ተቋም የህክምና ሪፖርት ስርዓቱን ዲጅታላይዝድ ለማድረግ የተያዘውን ዕቅድ ለማሳካትና እንደ ዕዝ ቀልጣፋ የመረጃ ልውውጥ ስርዓት ለመዘርጋት ከየክፍለጦሩ የተውጣጡ የህክምና ዳታ ሰራተኞችን እያሰለጠነ ነው።
በስልጠና አሰጣጥ ስነ-ሰርአቱ ላይ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት የዕዙ ጤና መምሪያ ሃላፊ ሌተናል ኮሎኔል ፍስሃ ፈንታው ጤና መምሪያው ከአይሲቲ ክፍሉ ጋር ትስስር ፈጥሮ ስራዎችን በጋራ እየሰራ እንደመጣ አስታውሰው፤ በየዘርፉ አሰራርን ለማዘመን በቅንጅት የሚደረጉ የጋራ ጥረቶች ለዘመናዊ ተቋሙ ግንባታ ጉልህ ሚና እዳላቸው ተናግረዋል።
ስልጠናው የሰው ሃይልን በኮምፒውተር እውቀት አሰልጥኖ በማብቃት ዘመኑን የዋጀ የቴክኖሎጅ ሲስተም ለመዘርጋትና በዳታ ቤዝ የታካሚን የህክምና ታሪክ ተከታትሎ በመሰነድ ሙያተኛው በየደረጃው የሚደረገውን የኢንፎርሜሽን ልውውጥና አመራሩ ግንዛቤ የሚወስድበትን የሪፖርት ስርዓት ግልፅና ቀልጣፋ ለማድረግ ያስችላል ብለዋል።
የዕዙ አይሲቲ መሰረተ ልማት ቡድን መሪ ሻለቃ ካልአዩ አሸብር በበኩላቸው ተቀናጅተው በመስራትና በዘርፉ ላይ ያላቸውን እውቀት ለሰልጣኙ በማጋራት በተለይም የዳታ ሰራተኛውን የኮምፒውተር እውቀት ለማበልፀግና የዳታ አያያዝና አጠቃቀም ስርአቶችን በማዘመን ሚስጥራዊነቱ የተጠበቀ የመረጃ ልውውጥ ስርአት መተግበር የሚችል የሰው ሃይል ለመፍጠር የሚያስችል ስልጠና መሆኑን አስታውቀዋል።
ሰልጣኞች በበኩላቸው የተመደቡበት የስራ ሃላፊነት ከፍተኛ ጥንቃቄና ትጋት የሚጠይቅ መሆኑን በመግለፅ በስልጠና የሚያገኙትን ተደማሪ አቅም ወደ ተግባር በመለወጥ በቀጣይ ሠራዊቱን የበለጠ ለማገልገል ቁርጠኛ መሆናቸውን ተናግረዋል።
ዘጋቢ ኤፍሬም አድማሱ
ፎቶ ግራፍ ሚኪያስ እስክንድር
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት
https://dfmc.mod.gov.et/
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0
https://www.facebook.com/fdredefense.official

❤18👍14👏2
የኢትዮጵያ ብሔራዊ መከላከያ ኮሌጅ የ5ኛ ባች ተማሪዎችን ማሰልጠን ጀመረ፦
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት መስከረም 11 ቀን 2019 ዓ.ም
የኢትዮጵያ ብሔራዊ መከላከያ ኮሌጅ በ2019 ዓ.ም የትምህርት ዘመን በፀጥታና ደህንነት ጉዳዮች በስትራቴጂክ አመራርነት የሚያሰለጥናቸውን የ5ኛ ባች ተማሪዎች ተቀብሎ ለማስተማር የመክፈቻ ፕሮግራም አካሂዷል።
በዕለቱ በክብር እንግድነት የተገኙት በመከላከያ የሰው ሃብት አመራር ዋና መምሪያ የስንብትና ቅጥር መምሪያ ሃላፊ ብርጋዲየር ጄነራል ግርማ ፈዬ የሀገራችን የመከላከያ ተቋም አቅም መገንባት የሚችሉ ከፍተኛ አመራሮች እንዲሁም የፌዴራልና የክልል የፀጥታ ደህንነት ሃይሎች በተጨማሪም ከተለያዩ ሀገራት የተወጣጡ ከፍተኛ ወታደራዊ አመራሮች መሳተፋቸው ኮሌጁ በቀጣናው እና በዓለም አቀፍ ደረጃ በስትራቴጂክ ጥናትና አመራር ዘርፍ እያበረከተ ያለውን አስተዋፅኦ የበለጠ የሚያጎላ ነው ብለዋል።
የኮሌጁ አዛዥ ተወካይ ኮሎኔል ደነቀ ደምሴ ይህ የ5ኛ ባች የትምህርት መርሃ-ግብር በተለይም በወቅታዊ የቀጠናው የፀጥታ ሁኔታዎች፣ በስትራቴጂክ አስተሳሰብ፣ በደህንነት አስተዳደር እና በጂኦ-ፖለቲካዊ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ጥልቅ የፖሊሲ ሃሳብ ማመንጨት የሚችሉ አመራሮችን በማስተመር ሀገራዊ ጥቅምን ማስጠበቅ የሚችል አመራር ለመፍጠር ሰፊ መደላድል የሚፈጥር መሆኑን ገልፀዋል።
ዘጋቢ አሰፉ ግርማይ
ፎቶግራፍ ኢፍቱ ቢራቱ

❤17👍10👏2🕊2
የሠላም ምሶሶ የሆነው የኢትዮጵያ ሠራዊት
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት መስከረም 11 ቀን 2019 ዓ.ም
ኢትዮጵያ በረጅሙ የታሪክ ጉዞዋ ሉዓላዊነቷን፣ ነፃነቷንና ሀገራዊ ማንነቷን አሥጠብቃ የኖረች ሀገር ናት። ይህ ጉዞ በድልና በፈተና፣ በመስዋዕትነትና በጽናት የተገኘ ነው። በዚህ ታሪካዊ ሂደት ሠራዊት የሀገር ሉዓላዊነት ዘብ፣ ጋሻ ሆኖ የተሰጠውን ተልዕኮ በድል ሲወጣ ቆይቷል። ዛሬም የኢትዮጵያ ሠራዊት ይህን ታሪካዊ ኃላፊነት በመሸከም የሀገርን ሉዓላዊነትና የሕዝብን ሰላም በመጠበቅ ተልዕኮውን እየተወጣ ይገኛል።
የኢትዮጵያ ሠራዊት ሀገር በምትፈልገው ጊዜ የሚቆም፣ ሕዝብን በኃላፊነት የሚያገለግልና ሉዓላዊነትን በቁርጠኝነት የሚጠብቅ ሃይል ነው። ለዚህ የተጠናከረ ውጤታማ የተልዕኮ አፈፃፀም ብቁ አመራር፣ የሰለጠነ የሰው ኃይል፣ የሥነ-ልቦና ጥንካሬ ያስፈልጋል። የእነዚህ አቅሞች ድምር ሠራዊቱ የተሰጠውን ተልዕኮ በውጤት እንዲፈፅም ያሥችለዋል።
ከሁሉም የኢትዮጵያ አካባቢዎችና ማኅበረሰቦች የመጡ አባላት በአንድ ዓላማ ተሠልፈው ለሀገር ሠላምና ልማት በጋራ ግዳጃቸውን የሚፈፅሙበት ለሰንደቅ ዓላማቸው ክብር የሚዋደቁበት ሀገርን በክብር የሚያሥቀጥሉበት ተቋም ነው መከላከያ።
የሠራዊቱ ጥንካሬ ከሕዝብ ጋር ባለው ትስስር ይጠናከራል። ሠራዊት ከሕዝብ የተለየ አካል ሳይሆን ከሕዝቡ የወጣና ለሕዝቡ የሚያገለግል ነው። ሕዝብ በሠራዊቱ ላይ እምነት ሲኖረው፣ ሠራዊቱም ሕዝቡን በክብር፣ በሕግና በኃላፊነት ሲያገለግል ይህ ትስስር ይጠናከራል። በችግር ጊዜ የሕዝብ ድጋፍ ለሠራዊቱ የሞራል አቅም ሲሆን፣ የሠራዊቱ ተጠያቂነት፣ ሙያዊ አፈጻጸምና ለሕዝብ ያለው ክብር ደግሞ የሕዝብን እምነት ያጠናክራል። ይህ የጋራ መተማመን ለሀገር ደህንነት ከፍተኛ አቅም ይፈጥራል።
ሠራዊቱ የተሰጠውን ግዳጅ በብቃት እየፈጸመ፣ ከሕዝብ ጋር ያለውን ትስስር እያጠናከረና የሀገርን ሉዓላዊነት በጽናት እየጠበቀ መቆሙ የሀገር ጥንካሬ ነው። ይህ ኃላፊነት የአንድ ዘመን ግዳጅ ሳይሆን ለትውልድ የሚሸጋገር ታሪካዊ ኃላፊነት ነው።
ስለዚህ ለሀገር ምሶሶ የሆነ ሠራዊት ማለት በፈተና ጊዜ የሚቆም፣ በግዳጅ ጊዜ የማይሸሽ፣ ከሕዝብ ጋር በእምነት የሚቆራኝና የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት በጽናት የሚጠብቅ ሠራዊት ነው። በመሆኑም የሀገር ክብር፣ የሕዝብ ደህንነትና የትውልድ ተስፋ የሚጠናከር ይሆናል።
በፍፁም ከተማ

❤21👏7🙏3👍1🥰1
በጠንካራ መሠረት ላይ የተገነባው መከላከያ ሠራዊት
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት መስከረም 11 ቀን 2019 ዓ.ም
ለአንድ ሀገር ዘላቂ ቀጣይነት መሠረት ከሚሆኑት ውስጥ ገለልተኛ ተቋማት ተጠቃሽ ናቸው፡፡
ወቅቶች ሲቀያየሩና መንግሥታት ሲለዋወጡ በጠንካራ መሠረት ላይ የተገነቡ እንደ ኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ያሉ የሀገርን ብሔራዊ ጥቅም፣ ሉዓላዊነትና የሕዝብን ደህንነት ለማስጠበቅ የሚተጉ ተቋማትን መገንባት አስፈላጊ ነው፡፡
ውግንናውን ለኢትዮጵያ ሕዝቦች ያደረገው መከላከያ ሠራዊት ሰላም የመጀመሪያ ምርጫው እንደመሆኑ ሀገር ከመጠበቅ ባሻገር ከሕዝብ ጎን በመቆም በተለያዩ አገልግሎቶች ላይ እገዛ ያደርጋል፡፡
ሀገርን ሊያጠቃ፣ ብሔራዊ ጥቅምን ሊነካ ለመጣ ጠላት ግን ዳር ድንበር ሊያስከብርና ሰላምን ሊያስጠብቅ፣ ሕይወትን እስከመገበር በሚደርስ ፅናት ከፊት ይሰለፋል፡፡
የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ከቀደሙት ጊዜያት ጀምሮ በተደራጀ አቅም፣ የሀገርን ዳር ድንበር ከማስጠበቅ ባሻገር ለቀጣናው ሰላም በማስከበር ሂደት ውስጥ ቀዳሚ ተሰላፊ ሆኖ እስከ ዛሬ ዘልቋል፡፡
ከኮሪያ ዘመቻ ጀምሮ በኮንጎ፣ በሱዳን አቢዬ፣ በደቡብ ሱዳንና በሶማሊያ የሰላም ማስከበር ተልዕኮዎች ላይ ተሳትፎ በማድረግ ለሰላም ያለውን ቁርጠኝነት አሳይቷል፡፡
በጀግንነት ብቻ ሳይሆን በጽናትና በሥነ ምግባር ባለው ታማኝነት የሚታወቀው መከላከያ ሠራዊት በእነዚህ የሰላም ማስከበር ተልዕኮዎች ውስጥ ባለው ተሳትፎ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት እውቅናን አግኝቷል፡፡
በእርግጥ ኢትዮጵያ ጀግንነት አዲስ ነገሯ አይደለም፤ ዓድዋና ካራማራ ላይ ሉዓላዊነቷን ለማስከበር ያደረገቻቸው ዘመቻዎች ስኬታማ የሆኑት በሠራዊቱና በሕዝቡ የጀግንነት ገድል ነው፡፡
ይህም ለሀገር መስዋዕት የመሆንና በጽናት የመቆም ባሕል እስከ ዛሬ ድረስ የሀገር መከላከያ ሠራዊት መለያ ሆኖ ቀጥሏል፡፡
በዘመናዊው ዓለም ወታደራዊ ጥንካሬን በዕውቀትና ቴክኖሎጂ ማሳደግ የሚጠይቅ በመሆኑ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ዛሬ ላይ በሰለጠነ የሰው ኃይል፣ በዘመናዊ የውጊያ ብቃትና ቴክኖሎጂዎች ራሱን አዘምኖ በዘመናዊ መሣሪያዎች በመታገዝ እየሰራ ይገኛል፡፡
በተጨማሪም በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ በመታገዝ የላቀ የሳይበር ደህንነትና የመገናኛ አውታሮች ዘመናዊ አቅሙን ገንብቷል፡፡
ኢትዮጵያ በተለያዩ ጊዜያት የውስጥና የውጪ ፈተናዎች ሲፈራረቁባት እንደመቆየቷ ጠላት ደጇን ሳይረግጥ እንዲቆይ ካደረጉት ውስጥ ዋነኛው የሀገር መከላከያ ሠራዊት ነው፡፡ በልበ ምሉዕነት ኢትዮጵያ ብርቱ ናት፤ ሉዓላዊነቷ አይደፈርም የምንለውም የማይደፈር ጠንካራ ሠራዊት ስላለን ነው፡፡
የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ጀግንነትን ከዘመናዊነት፣ ወታደራዊ ቴክኖሎጂዎችን ከዕውቀትና ስልጡን የሰው ኃይል ጋር አጣምሮ የያዘ በመሆኑ ሉዓላዊነትን በማስጠበቅ ካለው ሚና ባሻገር በዓለም አቀፍ ደረጃ ለሰላምና ሰብዓዊ ተግባራት የኢትዮጵያን የጀግንነትና የመልካምነት ገፅታ እያሳየ ይገኛል፡፡

❤20👍6
ከፀጥታና ደህንነት ተቋማት ለተውጣጡ አመራሮች ሥልጠና እየተሰጠ ነው
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት መስከረም 11 ቀን 2019 ዓ.ም
ወገኖቻችሁ በትከሻችሁ ላይ እያኖሩት ያለው ኃላፊነት እጅግ ከፍተኛ መሆኑን ልታውቁ ይገባል ሲሉ በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኢምባሲ ወታደራዊ አታሼ ኮሎኔል ማቲው ኮፕ ገለፁ ።
ከመከላከያ ሰራዊት ፣ ከፌደራል ፖሊስና ከብሄራዊ ደህንነት ለተውጣጡ አባላት ለሽብርተኝነት የሲቭል- ወታደራዊ ምላሾች ( Civili-Military Responses to Terrorism ) በሚል ርዕስ በመከላከያ መኮንኖች ክበብ ስልጠና እየተሰጠ ነው።
ስልጠናው በመከላከያ ውጪ ግንኙነትና ወታደራዊ ትብብር ዋና ዳይሬክቶሬት እና በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኢምባሲ ትብብር የተዘጋጀ ነው ። ስልጠናው ከአሜሪካ በመጡና በዘርፉ የዳበረ ልምድና እውቀት ባላቸው ወታደራዊና ሲቪል ሙያተኞች እየተሰጠ ይገኛል ።
በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኢምባሲ ወታደራዊ አታሼ ኮሎኔል ማቲው ኮፕ ባደረጉት ንግግር ሙያተኞች በበርካታ ዘርፎች፣ ሀገራት እና ግጭቶች ውስጥ ጥልቅ የሆነ ልምድ እንዳላቸው ጠቁመው ሰልጣኞቹ ከነሱ እንዲማሩና ማግኘት የሚችሉትን ሁሉ እውቀት እንዲያኙ ጠይቀዋል።
በመከላከያ ውጪ ግንኙነትና ወታደራዊ ትብብር ዋና ዳይሬክቶሬት የስልጠና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ሌተናል ኮሎኔል ምናሴ ኃይሉ በበኩላቸው የሽብርተኞች ድርጅቶች እና መረቦች ዘዴዎቻቸውን፣ መዋቅሮቻቸውን፣ የፋይናንስ ስልቶቻቸውን፣ የመመልመያ መንገዶቻቸውን እና የዘመናዊ ቴክኖሎጂ አጠቃቀማቸውን እየቀያየሩ መቀጠላቸውን ገልፀዋል።
ሌተናል ኮሎኔል ምናሴ ሃይሉ እነዚህ እየተቀየሩ ያሉ ሁኔታዎች ዝግጁነታችንን እንድንገመግም፣ ተቋሞቻችንን እንድናጠናክር እና በጋራና በብቃት የመመለስ አቅማችንን እንድናሻሽል የግድ ይለናል ሲሉም ተናግረዋል።
እንደሌተናል ኮሎኔል ምናሴ ገለፃ ፣ የስልጠናው ዓላማ ስለሚቀያየረው የሽብርተኝነት ስጋት ያለንን የጋራ ግንዛቤ ማጠናከር፣ የሲቪል-ወታደራዊ ቅንጅትን ማሳደግ፣ ዝግጁነትን እና የጋራ የምላሽ አቅምን ማሻሻል፣ የመረጃ ልውውጥን እና የቅንጅት ስልቶችን ማጠናከር፣ እንዲሁም ከሕግ የበላይነት እና ከሰብአዊ መብቶች ማክበር ጋር የተጣጣመ ሙያዊ ምላሽን ማሳደግ መሆኑን አብራርተዋል።
ዘጋቢ በላቸው ክንዴ
ፎቶ ግራፍ ገነት አወቀ

👍23❤22😁2