ትላንት ከሰአት በኋላ በተጠናቀቀው 47ኛው የአፍሪካ ክለቦች ሻምፒዮና ውድድር በሁለቱም ፆታ አል-ሃሊ የውድድሩ ሻምፒዮና ሲሆን ሀገራችንን የወከሉት መቻል እና መቐለ 70 እንደርታ በጥሩ ዲሲፕሊን እና በርካታ ልምዶችን በማግኘት ውድድራቸውን አጠናቀዋል።
ውድድሩ በእጅ ኳስ ቀጣይ በርካታ ስራዎችን መስራት እንደሚጠበቅብን የታየበት ከመሆኑም በላይ ከየሀገራቱ ክለቦች ጋር ብዙ ልምዶች መለዋወጥ የተቻለበት እንደሆነ እና ለ2019 ዓ.ም የኢትዮጵያ እጅ ኳስ ፕሪምየርሊግ ውድድር ላይ የተሻለውን መቻል የምናይበት አመት እንደሚሆን እምነታችን ነው ሲሉ ተወዳዳሪዎች ገልፀዋል።

የመከላከያ መቻል እጅ ኳስ ቡድን በዛሬው እለት ከአንጎላ ሉዋንዳ ዱባይ (UAE) አድርጎ በነገው እለት አዲስ አበባ ይገባል።
የዘገበው ገረመው ጨሬ ነው
