የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት መጋቢት 12 ቀን 2017 ዓ.ም
የመቻል ስፖርት ክለብ ቦርድ ሰብሳቢ ዶክተር ሰይፈ ጌታሁን ስፖርተኞችን አበረታትተዋል። አሁን እየተመዘገበ ባለው ውጤት በተለይም በ2ኛው የጆርካ አዲስ አበባ ክለቦች ሻምፒዮና በተገኘው ውጤት ቦርዱ ደስተኛ መሆኑን አንስተው ቀጣይ በሚደረጉ ውድድሮች ላይ የበለጠ ውጤት ማስመዝገብ ይገባችኋል ብለዋል።
በአትሌቲክሱ ዘርፍ እየተመዘገበ ባለው ወጤት ሌሎችም የክለቡ ቡድኖች ጥሩ መነሳሳት የሚፈጥራላችሁ በመሆኑ መደጋገፍ አለባችሁ ሲሉ ተናግረዋል።
የስራ አመራር ቦርዱ ለስፖርት ክለቡ አስፈላጊውን ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ መሆኑንም ዶክተር ሰይፈ ገልፀዋል።
ዘጋቢ ገረመው ጨሬ
ፎቶግራፍ ገረመው ጨሬ
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ቴሌግራም
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official

