የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት መጋቢት 14 ቀን 2017 ዓ.ም
በአዲስ አበባ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ስፖርት ለሁሉም አዘጋጅነት እየተሳተፈ የሚገኘው የመቻል ጤና እግር ኳስ ቡድን የዳግማዊ ሚኒልክ ሆስፒታልን 3ለ0 በሆነ ውጤት አሸንፏል።
የማሸነፊያ ጎሎቹን አምሳ አለቃ በሃይሉ አለባቸው ፣ አስር አለቃ ምህረትኣብ ማቲዮስ እና መሠረታዊ ወታደር እስክንድር ሰለሞን አስቆጥረዋል።
በሁለት ምድብ ተከፍሎ እየተካሄደ በሚገኘው የአንደኛ ዲቪዚዮን የጤና እግር ኳስ ቡድን መቻል ምድቡን በበላይነት በማጠናቀቅ ወደ ቀጣዩ ዙር አልፏል።

የመቻል ጤና እግር ኳስ ቡድን ካደረጋቸው ሰባት የምድብ ጨዋታዎች አምስቱን አሸንፎ ሁለቱን አቻ በመለያየት 17 ነጥብ እና 20 ተጨማሪ ጎል በመያዝ ምድቡን በአንደኝነት ማጠናቀቅ ችሏል።
የጤና እግር ኳስ ቡድን ከተለያዩ የመከላከያ ሠራዊት ክፍሎች ተወጣጥተው በመቻል ስፖርት ክለብ ደጋፊነት ተቋሙን በመወከል በኢፌዴሪ ባህል እና ስፖርት ሚኒስቴር እና በአዲስ አበባ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በሚያዘጋቻቸው ውድድሮች ላይ በመሳተፍ ውጤቶችን እያስመዘገበ ይገኛል።
የመቻል ጤና እግር ኳስ ቡድን ያለፈውን አመት በተወዳደረባቸው ሶስት ውድድሮች ሁሉንም ዋንጫዎችን በማሸነፍ የተቋሙን ስም ማስጠራት ችሏል።
ዘጋቢ ገረመው ጨሬ
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629…
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ቴሌግራም
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ