ብቃት ያላቸው ተተኪ ጀማሪ መኮንኖችን የማፍራቱ ጥረት ተጠናክሮ ቀጥሏል

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት መጋቢት 24 ቀን 2017 ዓ.ም

ብቃት ያላቸው ተተኪ ጀማሪ መኮንኖችን የማፍራቱ ጥረት ተጠናክሮ መቀጠሉን የሁርሶ አጭር ኮርስ ዕጩ መኮንን አዛዥ ኮሎኔል ከድር ጫጮ ተናግረዋል።

በመከላከያ ትምህርትና ስልጠና ዋና መምሪያ የሁርሶ አጭር ኮርስ ዕጩ መኮንን ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት ለመኮነንነት የሚያበቁ ስልጠናዎችን በመስጠት ብቁ ጀማሪ መኮንኖችን የማፍራቱን ጥረት አጠናክሮ መቀጠሉን የትምህርት ቤቱ አዛዥ ኮሎኔል ከድር ጫጮ ገልፀዋል ።

የአጭር ኮርስ ዕጩ መኮንን ትምህርት ቤት አዛዥ ኮሎኔል ከድር ጫጮ እንዳሉት ፣ የዕጩ መኮንኖችን የስልጠና ካሪኩለም አንዴ ብቻ ተቀርፆ የሚቀመጥ ባለመሆኑ ካሪኩለሙን በየጊዜው በማሻሻልና ጊዜውን የዋጀ  ስልጠና መሥጠት እየተቻለ ነው።

ዕጩ መኮንኖቹ ስልጠናቸውን አጠናቀው ሲወጡ የሚመሩትን ሠራዊት ማሰልጠንና ለግዳጅ ለማዘጋጀት የሚያስችል እውቀት እንዲጨብጡ ይደረጋል ያሉት አዛዡ በየትኛውም ጊዜና ሁኔታ የሚሰጣቸውን ውስብስብ ግዳጅ ሁሉ በድል የሚፈፅሙበትን ወታደራዊ ችሎታም እንዲጎናፀፉ ይደረጋል ብለዋል።

የአጭር ኮርስ ዕጩ መኮንን ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት አዛዥ ኮሎኔል ከድር ሰልጣኞች በራሳቸው ጥረትና እውቀት የመሰብሰቢያ አደራሽ መገንባታቸውንም ገልፀዋል።

ሰልጣኞቹ የመማር ማስተማር ሂደቱ ምቹና የተሳለጠ እንዲሆን በግቢው ውስጥ እሳር ከመትከል ጀምሮ ግቢውን ውብ ፣ማራኪና አስደሳች ለማደረግ በፈጠራ የታገዙ የተለያዩ ስራዎችን እየሰሩ መሆናቸውን ተናግረዋል።

በበላቸው ክንዴ

ኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ

https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 

https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ

https://www.facebook.com/fdredefense.official

ማስታወቂያ

No Posts Found

ክንውን

1
2
3
4
5
previous arrow
next arrow

ወቅታዊ አጀንዳ

s
ሠላምን በማፅናት ዕድገትና ብልፅግናን ለማረጋገጥ በቁርጠኝነት  እየተሰራ ነው። ዶክተር ጌድዮን ጢሞቲዎስ 
IMG_20250502_114207_631
ኢትዮጵያና ሞሮኮ በወታደራዊ ዘርፍ በትብብር  ለመስራት በሚያስችሏቸው ጉዳዮች ላይ ተወያዩ።
IMG_20250416_093208_823
የኢፌዴሪ ጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ክቡር ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ በሩዋንዳ የስራ ጉብኝት አደረጉ።
j,shuma
አመራር በትንሽ ኪሳራ ትልቅ ድል ማስመዝገብ የሚችለው ራሱን በማብቃት ዘመናዊ ሠራዊት ሲገነባ ነው። ሌተናል ጄኔራል ሹማ አብደታ
IMG_20250409_161558_051
የሚዲያ ስራችን በሠራዊታችን ተልዕኮና ግዝፈት ልክ መቃኘት ይኖርበታል።ሜጀር ጄኔራል እንዳልካቸው ወልደ ኪዳን
one
ስልጠና የመከላከያ ሠራዊቱን ሁለንተናዊ ብቃት በማሳደግ በኩል የሚጫወተው ሚና ከፍተኛ ነው  :-ሌተናል ጀኔራል አጫሉ ሸለመ

ስፖርት

ኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት

ለህገ መንግስቱ፣ ለሀገራችን መንግስትና ህዝቦች ፍፁም ታማኝ የሆነ፣ ጦርነትን የሚያቆም የልህቀትና የፍቅር ማዕከል የሆነ፣ በአስተማማኝ እና በብቃት በአገር አቀፍና በአለም አቀፍ ግዳጅ የሚያሳካ ዘመናዊ የመከላከያ ሰራዊት ማየት።

ማህበራዊ ሚዲያ