የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት መጋቢት 29 ቀን 2017 ዓ.ም
የሳንባ ምች በባክቴሪያ፣ በቫይረስ ወይም በፈንገስ ምክንያት የሚመጣ የአንዱ ወይም የሁለቱም ሳንባ ኢንፌክሽን ነው።
ማንኛውም ሰው በሳንባ ምች ሊጠቃ የሚችል ቢሆንም በከፍተኛ ሁኔታ ለበሸታው ተጋላጭ የሆኑት ዕድሜያቸው 65 እና ከዚያ በላይ የሆኑ አዋቂዎች፣ ከ2 ዓመት በታች የሆኑ ህጻናት፣ የጤና እክል ያለባቸው ሰዎች እና የሚያጨሱ ሰዎች ናቸው ተብሏል፡፡
በባክቴሪያ የሚመጣ የሳንባ ምች ምልክቶች፡- የከንፈር እና ጥፍር ሰማያዊ መሆን፣ ግራ መጋባት ወይም ድብርት (በተለይም በዕድሜ የገፉ ሰዎች ላይ)፣ (አረንጓዴ፣ ቢጫ ወይም ደም ያለበት) ፈሳሽ ያለው ሳል፣ ትኩሳት፣ ከባድ ላብ፣ የምግብ ፍላጎት ማጣት፣ ከፍተኛ ድካም፣ ቶሎ ቶሎ መተንፈስ፣ ፈጣን የልብ ምት፣ መንቀጥቀጥ ወይም ብርድ ብርድ ማለት፣ በረጅሙ መተንፈስ ወይም ማሳል፣ የደረት ህመም (ውጋት)፣ በተለይም በእንቅስቃሴ ወቅት እየተባባሰ የሚሄድ የትንፋሽ ማጠር አና ሌሎችም
በቫይረስ የሚመጣ የሳንባ ምች ምልክቶች፡- ራስ ምታት፣ የትንፋሽ እጥረት፣ የጡንቻ ህመም፣ ድካም እና ከባድ ሳል ይጠቀሳሉ፡፡
ብዙውን ጊዜ ህክምናው የሚደረገው በቅርብ ጊዜ ባለዎት የጤና ሁኔታ ሲሆን ፥ እንደ ቀዶ ጥገና፣ ጉንፋን እና መሰል ህመምን መሰረት በማድረግ ነውም ይላሉ የሕክምና ባለሙያዎች።
የሳንባ ምች ካለብዎ ሃኪም ያዘዘልዎትን መድሃኒት ሳያቋርጡ መውሰድ፣ በአግባቡ ምግብ መመገብ፣ ፈሳሽ በበቂ መውሰድ፣ እረፍት ማድረግ፣ ራስ ምታቱን መቆጣጠር እንዲሁም የኦክስጅን ህክምና መውሰድ በሽታው እንዳይባባስና ሌሎች ተጓዳኝ የጤና እክሎችን እንዳያስከትልብዎ ይረዳል፡፡
ጉንፋን የተለመደ የሳንባ ምች መንስኤ እንደሆነ የሚነሳ ሲሆን፥ ራስን ከጉንፋንና መሰል በሸታዎች መከላከል ይገባል፡፡ ተጋላጭነቱ ከዚህ ባስ ሲልም ማለትም ህጻናትና በእድሜ የገፉ ሰዎች የጉንፋን ወይም የሳንባ ምች ክትባት እንዲወስዱ ማድረግም እንደመፍትሄ ይወሰዳል፡፡
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ቴሌግራም
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ