የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት መጋቢት 29 ቀን 2017 ዓ.ም
የጦላይ ከፍተኛ ባለሌላ ማዕረግተኛ ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት 27ኛ ዙር ባለሌላ ማዕረግተኞችን እና 10ዙር መሠረታዊ ወታደሮችን በዛሬው ዕለት አሥመርቋል።
በምረቃ ስነ-ስርዓቱ ላይ በክብር እንግድነት የተገኙት የመከላከያ ትምህርትና ሥልጠና ዋና መምሪያ ሀላፊ ሌተናል ጄኔራል ይመር መኮነን ኢትዮጵያ ከሁሉም ጎረቤቶቿ ጋር በሰላምና በልማት ተሳስራ በጋራ ጥቅም ላይ የተመሠረተ ወዳጅነት ይዛ ለመቀጠል ፍላጎት ያላት ሀገር መሆኗን ተናግረዋል።
በተቋሙ የሠራዊታችንን አቅም በሁሉም ዘርፍ ለማጎልበት በስልጠና በሠው ሐይል ፣በትጥቅና በቴክኖሎጅ መዘመን ብቃት ያለው ሃይል በማብቃት እና በማዘጋጀት በአጭር ጊዜ የማድረግ አቅም እና የዝግጁነት ደረጃ ማሣደግ የሚያሥችል ሥራ እንዲሰራ መደረጉንም ገልፀዋል።
በምረቃ ስነ-ስርዓቱ ላይ የመከላከያ ትምህርትና ሥልጠና ዋና መምሪያ ሀላፊ ሌተናል ጄኔራል ይመር መኮነን፣ጄነራል መኮንኖች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
በሀይሌ ብርሃኑ
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ቴሌግራም
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official