የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ሚያዚያ 07 ቀን 2017 ዓ.ም
የኢፌዴሪ ጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ክቡር ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ እ.ኤ.አ ከኤፕሪል 13 እስከ 16 ቀን 2025 በሩዋንዳ የስራ ጉብኝት አድርገዋል።
ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ በሩዋንዳ መከላከያ ሠራዊት ኤታማዦር ሹም ጄነራል ሙባረክ ሙጋንጋ በክብር ዘብ የታጀበ ደማቅ አቀባበል የተደረገላቸው ሲሆን በሁለቱ ሀገራት መከላከያ መካከል የሁለትዮሽ የጋራ ውይይት ተካሂዷል።
በሁለትዮሽ የጋራ ውይይት ማጠቃለያ ላይ የሩዋንዳ መከላከያ ሠራዊት ኢታማዦር ሹም ጄኔራል ሙባረክ ሙጋንጋ እ.ኤ.አ. በመጋቢት ወር 2025 በኢትዮጵያ ባደረጉት የስራ ጉብኝት ወቅት በሁለቱ አገሮች መከላከያ መካከል በተፈረመው የመግባቢያ ስምምነት (MoU) ቀጣይ ትግበራ እና አፈፃፀም አቅጣጫ የሚያመለክት የመግባቢያ ስምምነት ተፈርሟል።
ጉብኝቱ የረጅም ጊዜ የሁለትዮሽ ትብብርን ለማጠናከር ትልቅ እንድምታ ያለው ሲሆን ሁለቱ አገራት በመከላከያ እና ሌሎች ተያያዥ ዘርፎች ላይ በአዳዲስ የትብብር መስኮች ለመሥራት እና የቀጠናውን ሰላም እና ደህንነትን ለማሳደግ ያላቸውን ቁርጠኝነት የሚያመላክት ነው።
ክቡር ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ በጉብኝታቸው ከሩዋንዳ ፕሬዝዳንት ከክቡር ፖል ካጋሜ ጋር በሁለቱ ሀገራት መከላከያ መኖር ስላለበት ግንኙነትና ትብብር በተመለከተ ውይይት ያደረጉ ሲሆን፤ እንዲሁም ከሩዋንዳው መከላከያ ሚኒስትር ጁቬናል ማሪዛሙንዳ ጋርም ተነጋግረዋል።
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
sDKCopw1FfTW2
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ቴሌግራም
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ