የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ግንቦት 28 ቀን 2017 ዓ.ም
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ግንቦት 28 ቀን 2017 ዓ.ም
ዛሬ ላይ የአለምን ህዝብ ወደ አንድ አካባቢ ያሰባሰበ መሠረታዊ ጉዳይ ነው ስፖርት። ስፖርት በሠራዊታችን ዘንድም የተለዬ ቦታ አለው። ከተፈለገው ግብ ለመድረስ፣ በአካል ብቃት ዳብሮ ለመገኘት፣ ግዳጅን በውጤት ለመፈፀም፣ ብቻ ሠራዊቱ ተልዕኮውን ቀለል አድርጎ በድል መፈፀም እንዲችል ስፖርት ዓይነተኛ ሚና አለው።
የእርስ በእርስ ዝምድናን ለማጠናከር፣ አሃዷዊ ፍቅርን ለማሣደግ፣ ግዳጅን በጋራ ለመወጣት፣ አብሮነትን ለማሥፋት ብቻ ስፖርት ለብዙ ነገሮች የሚረዳ በመሆኑ በሠራዊቱ ዘንድ በተለዬ መንገድ ትኩረት ተሠጥቶት የውድድር መድረኮች ይዘጋጃሉ በከፍተኛ ሞራል ውድድሮች ይካሄዳሉ።
ብቻም ሳይሆን እንደተቋም መከላከያን ወክለው ሊወዳደሩ የሚችሉ ብቃት ያላቸውን ስፖርተኞች ለመመልመልም ውድድሩ የራሱ የሆነ በጎ ገፅታ አለው።
ከውድድር በዘለለ በሠራዊቱ ዘንድ የሚካሄደው የዕለተ እረቡ የማሥ ስፖርትም ዘርፈ ብዙ አሥፈላጊነት ያለው በወዳጅነት ላይ የተመሠረቱ ውድድሮችን ለመፍጠር የሚያግዝ ነው።
የሠራዊቱ አባላትም ይህን ታሣቢ ያደረገ ከቁምነገሩ ጎን ለጎን እያዝናና አንድነትን የሚያጠናክር የእርስ በእርስ ውድድሮችን በእግር ኳስ ፣በመረብ ኳስ፣ በአትሌቲክስ፣ በገመድ ጉተታና በሌሎች የስፖርት ዓይነቶች ማካሄድ የዘወትር ተግባራቸው ነው።
በውብሸት ቸኮል
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ቴሌግራም
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ