ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ሰኔ 15 ቀን 2017 ዓ.ም
የኢፌዴሪ መከላከያ ዋር ኮሌጅ በ3ኛ ዙር መደበኛ ኮርስ ያሰለጠናቸውን ከፍተኛ መኮንኖች በዲፕሎማና በማስተርስ ዲግሪ ፕሮግራም በዛሬው ዕለት በደማቅ ሥነ-ሥርዓት አስመርቋል።
በምረቃ ሥነ- ስርዓቱ ላይ በክብር እንግድነት ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የጦር ሃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ፣ አገራችን ተልዕኮውን በላቀ ብቃት መፈፀም የሚችል በእውቀትና በክህሎት የጎለበተ ሠራዊት ያስፈልጋታል ተገንብቷልም ብለዋል።
ሠራዊቱ የታጠቀውን የዘመኑን ቴክኖሎጂ በወታደራዊ ኢንዱስትሪዎችና በጥናትና ምርምር በማሳደግ አዳዲስ ምርምሮችን ማዳበር እንደሚገባም አንስተዋል።
ተመራቂዎች በዚህ ወቅት አገራችን እያጋጠሟት ካሉ የውስጥ ግጭቶችና በቀጠናዉ ሊያጋጥሙ ከሚችሉ ትንታኔዎች በመነሳት ዝግጁነቱ የጎለበተና ሳይዋጋ ማሸነፍ የሚችል ሠራዊት ከመፍጠር አኳያ የጎላ ሚና መጫወት አለባችሁ ብለዋል።
አዳዲስ ስትራቴጂዎችን በመንደፍ በአስቸጋሪ ሁኔታዎች ውስጥ ውሳኔዎችን በመወሰን ተጣጣፊነትን ማሳደግ እንደሚበጅም አመላክተዋል።
ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ የተቋማችን አቅም ፈጣሪ አቅሞች እየጎለበቱ እንዲሄዱ የስልጠና ተቋማትን የውጊያና የውጊያ ድጋፍ አገልግሎቶችን የበለጠ ለማጠናከር ተመራቂዎች የቀሰማችሁትን እውቀት ከተቋሙ አሰራርና መመሪያዎች ጋር በማዋሃድ የላቀ ውጤት ማስመዝገብ ይጠበቅባችኋል ሲሉ አሳስበዋል።
የጦር ኃይሎች ጠቅላይ እታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ በስልጠናው ብላጫ ውጤት ላስመዘገቡ ተመራቂ ስትራቴጂክ አመራሮች ሰርተ-ፊኬትና ሽልማት አበርክተዋል
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ቴሌግራም
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ