119ኛው የኢትዮጵያ ሠራዊት ቀን የድል ሠራዊት” በሚል መሪ ቃል በሶማሊያ በሚገኘው ሴክተር ሦስትና በጦላይ ከፍተኛ ባለማዕረግተኛ ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት ተከብሯል።

የሴክተሩ ዋና አዛዥ ብርጋዲየር ጀነራል ሃሺም መሐመድ፣ ለሀገራችን ሉዓላዊነትና ደኅንነት፣ ለሕዝባችን ሰላምና ለአህጉራችን መረጋጋት በቁርጠኝነትና በጀግንነት እያገለገሉ ላሉ የሠራዊቱ አባላት ክብርና ምስጋና አቅርበው፣ በሰላም ማስከበር ተልዕኮዎች ላይ የተሰጣቸውን አደራ በብቃት በመወጣት፣ የ119 ዓመታትን የጀግንነት ታሪክ ማስቀጠልና የሠራዊቱን ሙያዊ ብቃት ማጠናከር እንደሚገባ አሳስበዋል።
