በዘመናዊ ጦር ሠራዊት ግንባታ ኢትዮጵያ የረጅም ዘመን አኩሪ ታሪክ ያላት ሀገር ናት። ጀነራል ይመር መኮንን

“የድል ሠራዊት”በሚል መሪ ቃል 119ኛው የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ቀን በሁርሶ ዕጩ መኮንን ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት በተለያዩ ዝግጅቶች ተከብሯል። በዕለት የተገኙት የመከላከያ ትምህርትና ስልጠና ዋና መምሪያ ሃላፊ ጀኔራል ይመር መኮነን፤ሀገራት የራሳቸውን ሉአላዊነት ለማስጠበቅ የጋራ ጥቅማቸውን ለማስከበር እንደየ አቅማቸው የጦር ሠራዊት ሲገነቡ መኖራቸውንና ከነኝህ ጥቂት ሃገራት መካከል በዘመናዊ ጦር ሠራዊት ግንባታ ታሪክ ሃገራችን ኢትዮጵያ የረጅም ዘመን አኩሪ ታሪክ ያላት መሆኗን ገልፀዋል።

የሠራዊት ቀንን ስናከብር ከቀደምት አባቶቻችን የተረከብናትን ሃገር ክብርና ሉአላዊነቷን ከየትኛውም ጊዜ በተለየ ሁኔታ ለማስጠበቅ ዳግም ቃል ኪዳናችንን በማደስ ሊሆን ይገባል ያሉት ጀኔራል ይመር መኮነን፤ ፈተናዎችን በድል እየተወጣን መጥተናል፤በድል የመወጣታችን ሚስጢርም ለአንድ ዓላማ የቆምን ህብረ ብሄራዊ ሠራዊት በመሆናችን ነው ብለዋል።

በብዓሉ የተንፀባረቀው ዋና መልዕክት፣የሠራዊቱን የቀድሞ ጀግኖች ታሪክ ማስታወስ ብቻ ሳይሆን ያንን ታሪክ በዘመናዊ ዕውቀት፣በተሻለ ስልጠና በሙያዊ ብቃትና በጠንካራ አመራር ማስቀጠል እንደሚገባ የሚያስታውስ ነው ያሉት ጀኔራል መኮንኑ፤ይህንን የሠራዊቱ የታሪክ አደራ በተግባር ለማስቀጠል በትምህርትና በስልጠና ላይ የምትገኙ ዕጩ መኮንኖች በዲስፕሊን ላይ መስራት እንደሚገባም አሳስበዋል።

ዛሬ ለቆምንለት መሰረቱ ጥንት አባቶቻችን የከፈሉት መስዋዕትነት ያስቀመጡልንን አሻራ ሁሌም በክብር ሊታወስ ይገባል ያሉት ደግሞ የሁርሶ ዕጩ መኮነን ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት አዛዥ ኮሎኔል ከድር ጫጮ ሲሆኑ፤ቀኑን ስናስታውስ ጦርነትን ተዋግቶ ማሸነፍ ብቻ ሳይሆን አስቀድሞ ከሩቅ ማስቀረት በሚቻል ደረጃ የዝግጁነት አቅማችንን ማረጋገጥ ይኖርብናል ብለዋል።

ኮሎኔል ከድር ፣የሠራዊት ቀንን ስናከብር በዝማሬያችን እንደምንገልፀው ምንም አይነት ምድራዊ ፈተና ቢገጥመንም ለጠላት የማንበገር ጀግና ሠራዊት መሆናችንን ያስመሰከርንበት እና ለመጪው ትውልድም የተከበረችና የታፈረች ሃገር ለማስረከብ ቃላችንን የምናድስበት ዕለት ነው ብለዋል።

ወቅታዊ አጀንዳ

photo_2026-10-25_07-18-37
ለህወሃት አምስተኛ ዕድል አንሰጠውም - ክቡር ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ
photo_2026-10-25_07-35-07
መከላከያ የሀገራችንን የኢኮኖሚ ዕድገት፣ የህዳሴ ጉዞና ዘላቂ ሰላም የሚያስጠብቅ ዋስትናችን ነው::  አቶ መሃመድ እድሪስ
photo_2026-10-25_07-53-26
የኢትዮጵያ የታጠቀ ኃይል በየዘመናቱ ታሪክ እየሠራ ያለፈ ነው:: ጄኔራል ዓለምእሸት ደግፌ
photo_2026-10-25_08-18-34
ለትውልድ የሚሸጋገር ታሪክ እየሰራን መጓዛችንን እንቀጥላለን።    ሌተናል ጄኔራል ብርሃኑ በቀለ
photo_2026-10-25_08-24-55
የኢትዮጵያ ሠራዊት አይበገሬነቱን በተግባር የሚሳይ አስተማማኝ የድል ሠራዊት ነው። ሌተናል ጀኔራል ዘውዱ በላይ
photo_2026-10-26_04-32-04
በዘመናዊ ጦር ሠራዊት ግንባታ ኢትዮጵያ የረጅም ዘመን አኩሪ ታሪክ ያላት ሀገር ናት። ጀነራል ይመር መኮንን

ስፖርት

ኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት

ለህገ መንግስቱ፣ ለሀገራችን መንግስትና ህዝቦች ፍፁም ታማኝ የሆነ፣ ጦርነትን የሚያቆም የልህቀትና የፍቅር ማዕከል የሆነ፣ በአስተማማኝ እና በብቃት በአገር አቀፍና በአለም አቀፍ ግዳጅ የሚያሳካ ዘመናዊ የመከላከያ ሰራዊት ማየት።