የኢትዮጵያ የታጠቀ ኃይል ታሪክ ዘመናትን ያስቆጠረ እና በየዘመናቱም ታሪክ እየሠራ ያለፈ ነው ሲሉ የኢፌዴሪ ጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ወታደራዊ አማካሪ እና የተኩስ አመራር ኃላፊ ጄኔራል ዓለምሸት ደግፌ ተናገሩ፡፡
“የድል ሠራዊት” በሚል መሪ ቃል በተከበረው 119ኛው የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ቀን መርሃ ግብር ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት ጄኔራል ዓለምእሸት ደግፌ 119ኛ የሠራዊት ቀን ስናከብር የዘመናዊ ሠራዊት ግንባታ መሰረት የተጣለበትን ዕለት ለመጥቀስ እንጂ፤ ይህ ቁጥር እንደ ሀገር የሚመጥን እንዳልሆነ በማመን ነው ብለዋል፡፡

ጄነራል ዓለምእሸት ደግፌ ህዝባችን ህልውናውን ያቆየው አንድነቱን እየጠበቀ ከውጪ የሚነሱ ኃይሎችን ተባብሮ በመምታቱ እንደሆነ ገልፀዋል፡፡
ሠራዊቱ ኢትዮጵያን ለማቆየት ከፍተኛ መስዋዕትነት የከፈለ ኃይል መሆኑን ጠቁመው፤ አንዳንድ ጊዜ በውጪ በሌላ ጊዜ ደግሞ በሀገር ውስጥ ጽንፈኛ ኃይሎች የመበተን አደጋ ማስተናገዱንም ተናግረዋል፡፡
የለውጡ መንግሥት ወደ ስልጣን ከመጣ በኋላ የቀደሙት ትውልዶች ሠራዊትና የወቅቱ ጦር ኃይል ኢትዮጵያ ለመከለካል እየከፈለ ያለውን ዋጋ በእኩል መታየት እንዳለበት መወሰኑን አብራርተዋል፡፡

በዚህም ላለፉት ከመቶ ዓመታት በላይ አኩሪ ገድል ሲፈጽም የቆው መለዮ ለባሽ በቅብብሎሽ ያስረከበን ተግባር ነውና የጋራ ቀን ተደርጎ ከለውጡ ወዲህ በተከታታይነት እየተከበረ እንደሚገኝ አመልክተዋል፡፡
የዘንድሮውን በዓል በግንባርና በደጀን ሀገራችንን፣ ህዝባችንን እና መንግሥታችን እያኮራ የሚገኘው ሠራዊት በያለበት በዓሉን እንደሚያከብር ገልጸዋል፡፡
