መከላከያ የሀገራችንን የኢኮኖሚ ዕድገት፣ የህዳሴ ጉዞና ዘላቂ ሰላም የሚያስጠብቅ ዋስትናችን ነው::  አቶ መሃመድ እድሪስ

119ኛው የመከላከያ ሠራዊት ቀን የድል ሠራዊት በሚል መሪ ቃል ዛሬ  በደማቅ ሥነ ሥርዓት ተከብሯል። በዚሁ ክብረ በዓል ላይ የመከላከያ ሚኒስትሩ አቶ መሃመድ እድሪስ መልዕክት አስተላልፈዋል።

በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭ ሀገራት የኢትዮጵያን ዳር ድንበር በጽናት ለመጠበቅ፣ ዘላቂ ሰላምና ጸጥታን ለማስፈን፣ እንዲሁም የሕዝባችንን ሁለንተናዊ ደህንነት ለማረጋገጥ በተለያዩ የግዳጅ ግንባሮች ላይ ለሚገኙ የመከላከያ ሠራዊት አባላት የሚከፍሉትን እስከ ሕይወት የሚደርስ ውድ መስዋዕትነት በከፍተኛ ሀገራዊ አክብሮት በመገንዘብ፣ በዚህ ታሪካዊ  ቀን ላቅ ያለ ምስጋና አቅርበዋል።

የዘንድሮውን የመከላከያ ሠራዊት ቀን “የድል ሠራዊት” በሚል መሪ ቃል ስናከብር፣ በጽናትና በጀግንነት የታነጸው ሠራዊታችን የሀገራችንን ህልውና የተፈታተኑ በርካታ ፈተናዎችን ድል በማድረግ፣ የኢትዮጵያን ነፃነትና ታሪካዊ ኩራት በተግባር ያስመሰከረ እውነተኛ የድል ባለቤት ሆኖ መቀጠሉን ገልፀዋል።

ሠራዊቱ የሀገራችንን ህልውና ለማፍረስ ከውስጥና ከውጭ የተሸረቡ አጥፊ ሴራዎችንና የሽብር እቅዶችን በበሰለ ስትራቴጂያዊ አመራር፣ በላቀ ወታደራዊ ዲሲፕሊን፣ በዘመናዊ ቴክኖሎጂና በሚደነቅ የውጊያ ብቃት መክቶ በማክሸፍ፣ የሀገራችንን ዳር ድንበርና የሕዝባችንን አንድነት በአስተማማኝ ሁኔታ መጠበቁንም ሚኒስትሩ አስገንዝበዋል።

በተካሄደው ጥልቅና አጠቃላይ የሪፎርም ሥራ፣ ተቋማችን በምድር፣ በአየርና በሳይበር ምህዳሮች ያለው ሁለንተናዊ የውጊያና የደህንነት አቅም በአስተማማኝ ደረጃ ላይ ይገኛል ያሉት ሚኒስትሩ ዛሬ ላይ ሠራዊታችን በዘመናዊ የጦር መሳሪያዎች፣ በሰው ሰራሽ አስተውሎትና በቴክኖሎጂ ምጥቀት፣ በከፍተኛ የስነ-ልቦና ዝግጁነት ላይ መገኘቱንም አረጋግጠዋል።

አቶ መሃመድ እድሪስ ተቋሙ የሕዝብንና የሀገርን ህልውና ብቻ ማዕከል አድርጎ የሚንቀሳቀስ፣ የሀገራችንን የኢኮኖሚ ዕድገት፣ የህዳሴ ጉዞና ዘላቂ ሰላም የሚያስጠብቅ ዋስትናችን እነደሆነም አሥገንዝበዋል። በርካታ ፈተናዎችንና ማዕበሎችን አልፎ ራሱን በዘመናዊ ወታደራዊ ሳይንስ ያደሰው ሠራዊት፣ ማንኛውንም ዓይነት የውስጥ አጥፊነትና የውጭ ትንኮሳ በጥበብና በብቃት የማክሸፍ አቅሙን በተግባር እንዳረጋገጠም ተናግረዋል።

የእናት ሀገርን ክብርና ሉዓላዊነት ለማስከበር ሲሉ ውድ ሕይወታቸውን ሰጥተው ሀገር ያቆዩልንን የመከላከያ ሠራዊታችንን ሰማዕታት በታላቅ አክብሮት እናስባቸዋለን፤ የቀደሙት የከፈሉት ውድ መስዋዕትነት የዛሬው ህልውናችንና የነገው ብሩህ ተስፋችን መሠረት ሆኖ ለዘላለም በልባችን ይኖራል ብለዋል።

ወቅታዊ አጀንዳ

photo_2026-10-25_07-18-37
ለህወሃት አምስተኛ ዕድል አንሰጠውም - ክቡር ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ
photo_2026-10-25_07-35-07
መከላከያ የሀገራችንን የኢኮኖሚ ዕድገት፣ የህዳሴ ጉዞና ዘላቂ ሰላም የሚያስጠብቅ ዋስትናችን ነው::  አቶ መሃመድ እድሪስ
photo_2026-10-25_07-53-26
የኢትዮጵያ የታጠቀ ኃይል በየዘመናቱ ታሪክ እየሠራ ያለፈ ነው:: ጄኔራል ዓለምእሸት ደግፌ
photo_2026-10-25_08-18-34
ለትውልድ የሚሸጋገር ታሪክ እየሰራን መጓዛችንን እንቀጥላለን።    ሌተናል ጄኔራል ብርሃኑ በቀለ
photo_2026-10-25_08-24-55
የኢትዮጵያ ሠራዊት አይበገሬነቱን በተግባር የሚሳይ አስተማማኝ የድል ሠራዊት ነው። ሌተናል ጀኔራል ዘውዱ በላይ
photo_2026-10-26_04-32-04
በዘመናዊ ጦር ሠራዊት ግንባታ ኢትዮጵያ የረጅም ዘመን አኩሪ ታሪክ ያላት ሀገር ናት። ጀነራል ይመር መኮንን

ስፖርት

ኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት

ለህገ መንግስቱ፣ ለሀገራችን መንግስትና ህዝቦች ፍፁም ታማኝ የሆነ፣ ጦርነትን የሚያቆም የልህቀትና የፍቅር ማዕከል የሆነ፣ በአስተማማኝ እና በብቃት በአገር አቀፍና በአለም አቀፍ ግዳጅ የሚያሳካ ዘመናዊ የመከላከያ ሰራዊት ማየት።