ለህወሃት አምስተኛ ዕድል አንሰጠውም – ክቡር ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ

119ኛ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ቀን “የድል ሠራዊት” በሚል መሪ ቃል በመከላከያ ጠቅላይ መምሪያ በደማቅ ሥነ ሥርዓት ተከብሯል። የዕለቱ የክብር እንግዳ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ክቡር ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

በዚህ የዲጂታል ዘመን ሀገር እናፈርሳለን የሽግግር መንግስት እንሰይማለን ብለው የሚለፉ ገንጣይ አሥገንጣዮች መቼም ቢሆን አይሳካላቸውም ያሉት ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ መስከረም 13 ቀን በሰሜን ወሎ ማጥቃት የጀመረው ጠላት በአሥር ቀናት ውስጥ በሚገባው ልክ ተመትቶ መንደፈራ መግባቱ አያድርስ የሚያሥብል ሽንፈት መሆኑንም ተናግረዋል።

ህገ ወጡ ህወሃት አራት ጊዜ ጦርነት ቀስቅሶ በሚገባው ልክ ተመትቶ መጥፋቱን የገለፁት ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ቀጣይም አምሥተኛ ልሞክር ብሎ ቢፍጨረጨር እንኳ በምንም ዓይነት ታዕምር ጊዜ እና ዕድል እንደማያገኝ ገልፀዋል።

የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት በውስጥ የተደራጁ ሰባት  የትብብር ቡድኖችን እንዲሁም ከጀርባቸው የቆሙ ሦስት የውጭ ኃይሎችን በድል ማሸነፉን የገለፁት ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ህወሃት መከላከያን አፈርሳለሁ የሚል የተሳሳተ ግምገማ ይዞ ወደ ጦርነት ቢገባም በጥቂት ቀናት ተመትቶ ደንበር ተሻግሮ ኤርትራ መግባቱን አውስተዋል።

መቼም ቢሆን መከላከያ ሠራዊት ጠላትን ያፈርሳል እንጅ በፍፁም አይፈርስም ሲሉ ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ በመከላከያ ሠራዊት ላይ ያላቸውን ሙሉ እምነትም ገልፀዋል።

ሁለቱም የውኃ አካላት ለቀጣናው ሀገራት በበቂ ሁኔታ የሚበቃ መሆኑ እየታወቀ እኛ ብቻ እንጠቀም የሚለው የመጠቅለል ፍላጎት ስህተት መሆኑን የተናገሩት የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ የዓባይ ውኃ የኢትዮጵያ የተፈጥሮ ፀጋ መሆኑን እና ቀይ ባህርም ኢትዮጵያዊያን እንዲገለገሉበት የተፈጠረ ባህር መሆኑን በአጽንኦት ገልጸዋል።

በክብረ በዓሉ ላይ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ፣ የመከላከያ ሚኒስትሩ አቶ መሃመድ እድሪስ፣ የብሄራዊ መረጃ ደህንነት ዳይሬክተር አምባሳደር ሬዳዋን ሁሴን ፣የቀድሞ ጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹሞች ጄኔራል ሳሞራ የኑስና ሌተናል ጄኔራል ፃድቃን ገብረ ተንሳይ፣ የህብረተሳባዊት ኢትዮጵያ ጀግና ሜዳይ ተሸላሚ ብርጋዲየር ጄኔራል ተስፋዬ ሀብተ ማርያም ፣የመንግስት ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች፣ ከፍተኛ የጦር መኮንኖች፣ የወዳጅ ሀገራት ወታደራዊ አታሼዎች እና ሌሎች ተጋባዥ እንግዶች ተገኝተዋል።

ወቅታዊ አጀንዳ

photo_2026-10-25_07-18-37
ለህወሃት አምስተኛ ዕድል አንሰጠውም - ክቡር ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ
photo_2026-10-25_07-35-07
መከላከያ የሀገራችንን የኢኮኖሚ ዕድገት፣ የህዳሴ ጉዞና ዘላቂ ሰላም የሚያስጠብቅ ዋስትናችን ነው::  አቶ መሃመድ እድሪስ
photo_2026-10-25_07-53-26
የኢትዮጵያ የታጠቀ ኃይል በየዘመናቱ ታሪክ እየሠራ ያለፈ ነው:: ጄኔራል ዓለምእሸት ደግፌ
photo_2026-10-25_08-18-34
ለትውልድ የሚሸጋገር ታሪክ እየሰራን መጓዛችንን እንቀጥላለን።    ሌተናል ጄኔራል ብርሃኑ በቀለ
photo_2026-10-25_08-24-55
የኢትዮጵያ ሠራዊት አይበገሬነቱን በተግባር የሚሳይ አስተማማኝ የድል ሠራዊት ነው። ሌተናል ጀኔራል ዘውዱ በላይ
photo_2026-10-26_04-32-04
በዘመናዊ ጦር ሠራዊት ግንባታ ኢትዮጵያ የረጅም ዘመን አኩሪ ታሪክ ያላት ሀገር ናት። ጀነራል ይመር መኮንን

ስፖርት

photo_2026-10-25_07-18-37
ለህወሃት አምስተኛ ዕድል አንሰጠውም - ክቡር ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ
photo_2026-10-25_07-35-07
መከላከያ የሀገራችንን የኢኮኖሚ ዕድገት፣ የህዳሴ ጉዞና ዘላቂ ሰላም የሚያስጠብቅ ዋስትናችን ነው::  አቶ መሃመድ እድሪስ
photo_2026-10-25_07-53-26
የኢትዮጵያ የታጠቀ ኃይል በየዘመናቱ ታሪክ እየሠራ ያለፈ ነው:: ጄኔራል ዓለምእሸት ደግፌ
photo_2026-10-25_08-18-34
ለትውልድ የሚሸጋገር ታሪክ እየሰራን መጓዛችንን እንቀጥላለን።    ሌተናል ጄኔራል ብርሃኑ በቀለ
photo_2026-10-25_08-24-55
የኢትዮጵያ ሠራዊት አይበገሬነቱን በተግባር የሚሳይ አስተማማኝ የድል ሠራዊት ነው። ሌተናል ጀኔራል ዘውዱ በላይ
photo_2026-10-26_04-32-04
በዘመናዊ ጦር ሠራዊት ግንባታ ኢትዮጵያ የረጅም ዘመን አኩሪ ታሪክ ያላት ሀገር ናት። ጀነራል ይመር መኮንን

ኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት

ለህገ መንግስቱ፣ ለሀገራችን መንግስትና ህዝቦች ፍፁም ታማኝ የሆነ፣ ጦርነትን የሚያቆም የልህቀትና የፍቅር ማዕከል የሆነ፣ በአስተማማኝ እና በብቃት በአገር አቀፍና በአለም አቀፍ ግዳጅ የሚያሳካ ዘመናዊ የመከላከያ ሰራዊት ማየት።