የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት መጋቢት 12 ቀን 2017 ዓ.ም
የሰሜን ምዕራብ ዕዝ ዋና አዛዥ ሌተናል ጄኔራል ብርሃኑ በቀለ ለዕዙ አመራሮች የብቃትና ክህሎት ማሳደጊያ ስልጠና ላይ ስልጠና በሰጡበት ዕለት የባዕዳን ህልም ዕና ሀሳብ በሕብረ ብሄራዊ ሰራዊቱ መክኗል ሲሉ ተናግረዋል።
አዛዡ የሠራዊቱን አዕምሮአዊ ፣ አካላዊ እና ስሜታዊ ብቃቱን ለማሳደግ ተቋሙ የያዘውን ፕሮፌሽናል ሠራዊት የመገንባት ሂደት ስልጠና ወሳኝ ሚና አለው ብለዋል።

ውግንናው ለህዝብ የሆነ በእሴት የተቀረፀ የሚወስን ፣ የሚፈፅም እና በየጊዜው የሚሻሻል ሠራዊት እንዲሁም ለታላቅ ሀገር እና ህዝብ የቆመ ጦርነትን የማስቀረት ብቃት ያለው ሀገር ተገዳ በጠላት እብሪትና በጦርነቱ አስፈላጊነት ወደጦርነት መግባት የግድ በሚልበት ጊዜ ተዋግቶ የሚያሸንፍ የሀገርን ሉአላዊነት የሚጠብቅና የሚከላከል የጋራ ተልዕኮውን በብቃት እና በተሳካ ሁኔታ የሚያረጋግጥ ሠራዊት ኢትየጵያ እንዳላትም ተናግረዋል።

ዘጋቢ አንዱአለም ከፍያለው
ፎቶግራፍ አንዱአለም ከፍያለው
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ቴሌግራም
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official