ለጉንፋን ህመም ቀላል መፍትሄዎች

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት መጋቢት 15 ቀን 2017 ዓ.ም

አብዛኛዉ የጉንፋን ህመም ያላቸዉ ሰዎች የህክምና ባለሙያ ማየት ሳያስፈልጋቸዉ በቤታቸዉ ሆነዉ እራሳቸዉን ማከም ይችላሉ፡፡

እንፋሎት መታጠ ፎጣ/ማንኛዉንም ነገር ጭንቅላትዎ ላይ በመሸፈን እየፈላ ባለ ዉሃ እንፋሎቱን መታጠን፡፡ ይህ የመቆጥቆጥና የአፍንጫ መጠቅጠቅ ስሜቱን ለመቀነስ ይረዳል፡፡

ፈሳሽ በብዛት መጠጣት (የአልኮል መጠጥን አይጨምርም) ዉሃ፣ ጁስ/የፍራፍሬ ጭማቂና ሞቅ ያለ ሾርባ በብዛት መዉሰድ የሚከሰትብዎን የፈሳሽ እጥረት ለመከላከል ይረዳል በቂ እረፍት ማድረግየበሽታ መከላከል አቅምዎን ለማጎልበትና ቫይረሱን መዋጋት እንዲችሉ በቂ እንቅልፍ ያግኙ፡፡

አፍን ወደ ላይ ቀና አደርጎ ከጀርባ ወደ ኋላ ገለል በማለት ጥቂት ውሃ ወደ ጉሮሮ በማፍሰስ መጉመጥመጥ የጉሮሮ መከርከርና ማቃጠልን ለመከላከል ይረዳል። ለዚህ ደግሞ 1 የሻይ ማንኪያ ጨውን ለብ ባለ አንድ ኩባያ ውሃ በመቀላቀል ወደ ጉሮሮ ማንቆርቆር እና መጉመጥመጥ።

ከዚህ ባለፈም 1 የሻይ ማንኪያ የሎሚ ውሃና ማርን አንድ ላይ በማድረግ ከውሃው ጋር ቀላቅሎ መጠቀም፤ ውሃው ግን ለብ ያለ እንጅ የሚያቃጥል መሆን የለበትም። ሻይ በሎሚ እና በማር ቀላቅሎ መጠጣትም ይመከራል

ሻይን በሎሚ እና በማር መጠቀምዎ የአፍንጫ መደፈንና መታፈንን እና የጉሮሮ ህመምን ለማከም እንደሚረዳም ባለሙያዎች ይናገራሉ። ሾርባ በተለይም የአትክልት ሾርባዎችን መውሰድም ይመከራል፥ በጉንፋኑምክንያት የሚፈጠረውን የአፍንጫ መዘጋት በመክፈት በአግባቡ ለመተንፈስ ይረዳል።

ሞቅ ባለ ውሃ ገላን መታጠብ የአፍንጫ መደፈንን ያስወግዳል። ጉንፋን በታመሙ ጊዜ በሙቅ ውሃ መታጠብ አልያም ውሃን በማፍላት በጎድጓዳ ሳህን በማድረግ በፎጣ ነገር ተከናንቦ መታጠን። ከዚህ ጋር ተያይዞ በዚህ ወቅት መድሃኒት ቤት የሚሸጡና ለጉንፋን ማከሚያ የሚረዱ ኢዩካሊፕተስ የሚባሉጠብታዎችን ውሃው ላይ በማድረግ መጠቀም።

በጉንፋን የተያዘ አዋቂ ሰው ማርን ከሻይ ጋር ቀላቅሎ እንዲጠቀም ይመከራል። እድሜያቸው ከአንድ አመት በላይ ለሆኑ ህጻናት ደግሞ ከመኝታ በፊት በጥቂቱ መስጠት፤ በመኝታ ሰዓት እንዳይስሉ ይረዳቸዋልና።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ

https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-

sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 

https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ

https://www.facebook.com/fdredefense.official

ማስታወቂያ

No Posts Found

ክንውን

1
2
3
4
5
previous arrow
next arrow

ወቅታዊ አጀንዳ

s
ሠላምን በማፅናት ዕድገትና ብልፅግናን ለማረጋገጥ በቁርጠኝነት  እየተሰራ ነው። ዶክተር ጌድዮን ጢሞቲዎስ 
IMG_20250502_114207_631
ኢትዮጵያና ሞሮኮ በወታደራዊ ዘርፍ በትብብር  ለመስራት በሚያስችሏቸው ጉዳዮች ላይ ተወያዩ።
IMG_20250416_093208_823
የኢፌዴሪ ጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ክቡር ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ በሩዋንዳ የስራ ጉብኝት አደረጉ።
j,shuma
አመራር በትንሽ ኪሳራ ትልቅ ድል ማስመዝገብ የሚችለው ራሱን በማብቃት ዘመናዊ ሠራዊት ሲገነባ ነው። ሌተናል ጄኔራል ሹማ አብደታ
IMG_20250409_161558_051
የሚዲያ ስራችን በሠራዊታችን ተልዕኮና ግዝፈት ልክ መቃኘት ይኖርበታል።ሜጀር ጄኔራል እንዳልካቸው ወልደ ኪዳን
one
ስልጠና የመከላከያ ሠራዊቱን ሁለንተናዊ ብቃት በማሳደግ በኩል የሚጫወተው ሚና ከፍተኛ ነው  :-ሌተናል ጀኔራል አጫሉ ሸለመ

ስፖርት

ኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት

ለህገ መንግስቱ፣ ለሀገራችን መንግስትና ህዝቦች ፍፁም ታማኝ የሆነ፣ ጦርነትን የሚያቆም የልህቀትና የፍቅር ማዕከል የሆነ፣ በአስተማማኝ እና በብቃት በአገር አቀፍና በአለም አቀፍ ግዳጅ የሚያሳካ ዘመናዊ የመከላከያ ሰራዊት ማየት።

ማህበራዊ ሚዲያ