የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት መጋቢት 15 ቀን 2017 ዓ.ም
አየር ሃይል፣ ሳይበርና ሜካናይዝድን በማዘመን ወጊያን በመሳሪያ ቴክኖሎጅ እና በውሰን የሰው ሀይል የመጨረሰ አቅም ተገንብቷል ሲሉ የጦር ሃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ ተናግረዋል። የሜካናይዝድ ዕዝ ያሰለጠናቸውን የሜካናይዝድ ሙያተኞች በዛሬው ዕለት አስመርቋል።
በምረቃ ሰነ-ሰርዓቱ ላይ በክብር እንግድነት የተገኙት የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ፣በአዋሽ አርባ ወጊያና ቴክኒክ ትምህርት ቤት ሲሰለጥኑ የቆዩ የሜካናይዝድ ዕዝ ሙያተኞችን የተኩስ ወጤት ተመልክተዋል።

መከላከያ እንደ ግብ አስቀምጦ ካከናወናቸው የሪፎርም ስራዎች መካከል የመከላከያ ሠራዊቱን አቅም በክህሎት እና ዘመኑ ባፈራቸው ትጥቆች በራስ አቅም አዘምኖ ሠራዊቱ ማንኛውንም ግዳጅ በድል እንዲወጣ ማድረግ አንዱ አቅጣጫ እንደነበር አውስተው ይህም ውጤታማ በሆነ አግባብ በተግባር መረጋገጡን ገልፀዋል።
ዛሬ በሜካናይዝድ ዕዝ ሰልጣኞች የታየው ሁሉን አቀፍ የማድረግ አቅምና ብቃትም የተቋሙ እቅድ አንድ አካል መሆኑን አሰገንዝበዋል።ኢትዮጵያ በተለያዬ ዘመናት የገጠሟትን ፈተናዎች ሁሉ በድል መወጣት የቻለችው በጀግኖች ልጆቿ መሰዋዕትነት ነው ያሉት ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ይህ የአሸናፊነት ሰነ -ልቦና ዛሬም በእያንዳንዱ ወታደር ልቦና ወሰጥ መኖሩን ገልፀዋል።
መንግሰት በወሰደው የፀጥታ ተቋማትን የማደራጀትና የመገንባት ሰራ መከላከያ ዘመኑ ያፈራቸውን ዘመናዊ የጦር መሳሪያዎችን በራስ አቅም በማምረት በማስታጠቅና መጠቀምና መምራት የሚችል በተግባር
ተፈትኖ ያለፈ በቂ የሰው ሃይል መገንባቱንም አረጋግጠዋል።
ሜካናይዝዱን በማዘመንና በማቀናጀት ውጊያን በዘመናዊ የጦር መሳሪያ በትንሽ የሰው ሃይል ለመጨረስ ትኩረት ተሰጥቶ መሰራቱንም ገልፀዋል ። ዛሬ የታየው ወጤትም ጠላቶቻችን ደጋግመው እንዲያስቡ የሚያደርግና ጦርነትን በሩቁ ለማስቀረት የሚያስችል መሆኑን ገልፀው ተቋሙን ያደራጀነውም አሁናዊ የአለም የጦርነት ባህሪን ግምት ውሰጥ በማስገባት ነው ብለዋል።
ማሩ ግርማይ
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ቴሌግራም
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ