የጦር መሳሪያ ማስተኮሽያ ሶፍትዌር ያበለፀጉ የፈጠራ ጥበበኞች

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት መጋቢት 15 ቀን 2017 ዓ.ም

መሠረታዊ ወታደር ዘላለም ቤዛነህ እና መሰረታዊ ወታደር ዳንኤል ሙልቀን ይባላሉ። ሁለቱ ወጣት ወታደሮች ምንም እንኳን የልጅነት መንገዳቸው የተለያየ ቢሆንም በሀገር ፍቅር ማዕበል የተሳሰሩ ጓደኛሞች ናቸው።

ሁለቱ መሠረታዊ ወታደሮች የጀግኖች ልጆች  በአባቶቻቸው የጀግንነት ታሪክ ተኮትኩተው ያደጉ ናቸው። የሀገር ፍቅር በደም ስራቸው ገብቶ ለወታደርነት ሙያ ያላቸው ክብር ከልጅነታቸው ጀምሮ ሲያብብ መኖሩን ይናገራሉ። ሁለቱም የማወቅ ጉጉት የሞላባቸው ማንኛውንም ነገር የመመራመር ፍላጎት ያላቸው ልጆች ናቸው። እንዴት እንደሚሰራ ለማወቅ ማንኛውንም ነገር መነካካት ይወዱ ነበር።ትምህርታቸውን በሚገባ ተከታትለው አጠናቀዋል። በተለይ ዳንኤል በኮምፒውተር ሳይንስ የመጀመሪያ ዲግሪውን በውጤት አጠናቋል። ነገር ግን የሀገር ፍቅርና የአባቶቻቸው የጀግንነት ታሪክ በልባቸው ውስጥ ነግሶ የተማሩበትን እውቀት ለሀገር ክብር ለመጠቀም ወሰኑ።

በአዋሽ አርባ ውጊያና ቴክኒክ ትምህርት ቤት ለሜካናይዝድ ስልጠና ሲገናኙ የጋራ ፍላጎታቸውና የሀገር ፍቅራቸው ወዲያውኑ አቀራረባቸው። በማሰልጠኛው ቆይታቸውም ከመደበኛ ስልጠናቸው ጎን ለጎን የቴክኒክ ችሎታቸውን በማጣመር የጦር መሳሪያ ማስተኮሽያ ሶፍትዌር አበለፀጉ ይህንንም ፈጠራ ለመሪዎቻቸው አቀረቡ ውጤታማነቱም ተረጋገጠ።

ይህ ሶፍት ዌር ለማሰልጠኛውም ለተቋሙም ትልቅ የፈጠራ ውጤት እንደሆነ የታመነበት ሲሆን ሁለቱንም በጀግንነታቸውና በፈጠራ ችሎታቸው ላበረከቱት አስተዋፅኦ በምረቃ ስነ-ስርዓታቸው ዕለት የሙሉ አስር አለቅነት ማዕረግ ከጦር ሀይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ ተበርክቶላቸዋል።እነዚህ ወጣት አሥር አለቆች የቴክኖሎጂ እውቀትንና የሀገር ፍቅርን በማጣመር ለአገራቸው እድገት አስተዋፅኦ ማድረግ እንደሚቻል በማሳየት አርአያነት ያለው ተግባር ለመከወን ችለዋል።

አሥር አለቃ ዘላለም ቤዛነህ እና አሥር አለቃ ዳንኤል ሙልቀን የተሰጠን ማዕረግ ከእድገቱ በተጨማሪ ከባድ ሀገራዊ ሀላፊነት በመሆኑ ለበለጠ የፈጠራ ስራ እንተጋለን ሲሉ አጫውተውናል።

አሥር አለቆቹ በጀግንነታቸው፣ በፈጠራ ችሎታቸውና በጓደኝነታቸው የሚታወሱ ለወጣት የሠራዊት አባላትም አርአያነት ያለው ተግባር የሰሩና ተቋማችንም የዕውቀት ማዕከል እንደሆነ ያመላከቱ ጀግኖች ናቸውና ነገም በዙ እንደሚሠሩ እምነታችን ነው።

በልደት አስረስ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ

https://youtube.com

@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 

https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ

https://www.facebook.com/fdredefense.official

ማስታወቂያ

No Posts Found

ክንውን

1
2
3
4
5
previous arrow
next arrow

ወቅታዊ አጀንዳ

s
ሠላምን በማፅናት ዕድገትና ብልፅግናን ለማረጋገጥ በቁርጠኝነት  እየተሰራ ነው። ዶክተር ጌድዮን ጢሞቲዎስ 
IMG_20250502_114207_631
ኢትዮጵያና ሞሮኮ በወታደራዊ ዘርፍ በትብብር  ለመስራት በሚያስችሏቸው ጉዳዮች ላይ ተወያዩ።
IMG_20250416_093208_823
የኢፌዴሪ ጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ክቡር ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ በሩዋንዳ የስራ ጉብኝት አደረጉ።
j,shuma
አመራር በትንሽ ኪሳራ ትልቅ ድል ማስመዝገብ የሚችለው ራሱን በማብቃት ዘመናዊ ሠራዊት ሲገነባ ነው። ሌተናል ጄኔራል ሹማ አብደታ
IMG_20250409_161558_051
የሚዲያ ስራችን በሠራዊታችን ተልዕኮና ግዝፈት ልክ መቃኘት ይኖርበታል።ሜጀር ጄኔራል እንዳልካቸው ወልደ ኪዳን
one
ስልጠና የመከላከያ ሠራዊቱን ሁለንተናዊ ብቃት በማሳደግ በኩል የሚጫወተው ሚና ከፍተኛ ነው  :-ሌተናል ጀኔራል አጫሉ ሸለመ

ስፖርት

s
ሠላምን በማፅናት ዕድገትና ብልፅግናን ለማረጋገጥ በቁርጠኝነት  እየተሰራ ነው። ዶክተር ጌድዮን ጢሞቲዎስ 
IMG_20250502_114207_631
ኢትዮጵያና ሞሮኮ በወታደራዊ ዘርፍ በትብብር  ለመስራት በሚያስችሏቸው ጉዳዮች ላይ ተወያዩ።
IMG_20250416_093208_823
የኢፌዴሪ ጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ክቡር ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ በሩዋንዳ የስራ ጉብኝት አደረጉ።
j,shuma
አመራር በትንሽ ኪሳራ ትልቅ ድል ማስመዝገብ የሚችለው ራሱን በማብቃት ዘመናዊ ሠራዊት ሲገነባ ነው። ሌተናል ጄኔራል ሹማ አብደታ
IMG_20250409_161558_051
የሚዲያ ስራችን በሠራዊታችን ተልዕኮና ግዝፈት ልክ መቃኘት ይኖርበታል።ሜጀር ጄኔራል እንዳልካቸው ወልደ ኪዳን
one
ስልጠና የመከላከያ ሠራዊቱን ሁለንተናዊ ብቃት በማሳደግ በኩል የሚጫወተው ሚና ከፍተኛ ነው  :-ሌተናል ጀኔራል አጫሉ ሸለመ

ኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት

ለህገ መንግስቱ፣ ለሀገራችን መንግስትና ህዝቦች ፍፁም ታማኝ የሆነ፣ ጦርነትን የሚያቆም የልህቀትና የፍቅር ማዕከል የሆነ፣ በአስተማማኝ እና በብቃት በአገር አቀፍና በአለም አቀፍ ግዳጅ የሚያሳካ ዘመናዊ የመከላከያ ሰራዊት ማየት።

ማህበራዊ ሚዲያ