የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት መጋቢት 17 ቀን 2017 ዓ.ም
በትጥቅም ሆነ በትጥቅ ግብዓቶች የመከላከያ ሠራዊቱን የዝግጁነት ደረጃ ለማሣደግ በውጤት እየሠራን ነው ሲሉ የመከላከያ ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ ግሩፕ ዋና ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው ሃይለማሪያም ተናገሩ
ቆየት በሚል ስያሜው የመከላከያ ኢንጂነሪግ ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን በሚል ሲጠራ የነበረው አሁን ላይ ተቋሙ በሚኒስትሮች ምክር ቤት በደንብ ቁጥር 567/2017 በመፅደቁ የመከላከያ ኢንጂነሪግ ኢንዱስትሪ ግሩፕ በመባል አድማሱን በማስፋት በርካታ ኢንዱስትሪዎችን አካቷል።
ለመከላከያ ሠራዊት የተለያዩ ትጥቆችን እና የትጥቅ ግብዓት ምርቶችን በማምረት እና የተለያዩ የኮሜርሻል ምርቶችን በማምረት እንደ ተቋም ብሎም እንደ ሀገር ብቸኛው ተቋም ከመሆኑ አንፃር ትልቅ የሃይል አቅም በመሆን ዘርፈ ብዙ በቴክኖሎጂ የታገዙ ተግባራትን እያከናዎነ እንደሚገኝ የመከላከያ ኢንጂነሪግ ኢንዱስትሪ ግሩፕ ዋና ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው ሃይለማሪያም ገልፀዋል።
መንግስትና ተቋሙ ለመከላከያ ኢንጂነሪግ ኢንዱስትሪ ግሩፕ ከፍተኛ ትኩረት በመስጠታቸው በሪፎርሙ አዳዲስ ዘመናዊ የቴክኖሎጂ ውጤቶችን በመጠቀም የምርትና ምርታማነትን በማምረት የሠራዊቱን የዝግጁነት አቅም በከፍተኛ ደረጃ ማሳደግ መቻሉን ዋና ዳይሬክተሩ ተናግረዋል።
የመከላከያ ኢንጂነሪግ ኢንዱስትሪ ግሩፕ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ሃብት አስተዳደር ዘርፍ ኮሎኔል ዩሃንስ ትኬሳ በበኩላቸው እየተመዘገበ ያለው ሁሉን አቀፍ ለውጥ ለተቋሙ ብሎም ለሀገራችን ከፍታ ያለው ሚና ከፍተኛ መሆኑን ገልፀዋል።
የመከላከያን ፍላጎት ለማሟላት የኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ ግሩፑ አመራርና ሠራተኛ በአንድ እስትንፋስ ምርትና ምርታማነትን በማሣደጉ ረገድ ሥራቸውን በአግባቡ በመፈፀም ሀገራዊ ተልዕኳቸውን በስኬት የመወጣቱን ሂደት አጠናክረው እንደሚቀጥሉም ኮሎኔል ዩሃንስ ተናግረዋል።
በመስከረም ብርሃኔ
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ቴሌግራም
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ