የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት መጋቢት 24 ቀን 2017 ዓ.ም
ዛሬ የአለምን ህዝብ ወደ አንድ መንደር ካሰባሰበው መሠረታዊ ጉዳይ አንዱ ስፖርት ነው። ስፖርት በሠራዊታችን ዘንድም የተለዬ ቦታ አለው። ከተፈለገው ግብ ለመድረስ በአካል ብቃት ዳብሮ ለመገኘት ግዳጅን በውጤት ለመፈፀም ብቻ ሠራዊቱ ተልዕኮውን ቀለል አድርጎ መፈፀም እንዲችል ስፖርት ዓይነተኛ ሚና አለው።
የእርስ በእርስ ዝምድናን ለማጠናከር አሃዷዊ ፍቅርን ለማሣደግ የሚረዳ በመሆኑ በሠራዊቱ ዘንድ ስፖርት በተለዬ መንገድ ትኩረት ተሠጥቶት የውድድር መድረኮች ይዘጋጃሉ በከፍተኛ ሞራል ውድድሮች ይካሄዳሉ።
ብቻም ሳይሆን እንደተቋም መከላከያን ወክለው ሊወዳደሩ የሚችሉ ብቃት ያላቸውን ስፖርተኞች ለመመልመልም ውድድሩ የራሱ የሆነ በጎ ገፅታ አለው።
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ቴሌግራም
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official