የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት መጋቢት 24 ቀን 2017 ዓ.ም
ብቃት ያላቸው ተተኪ ጀማሪ መኮንኖችን የማፍራቱ ጥረት ተጠናክሮ መቀጠሉን የሁርሶ አጭር ኮርስ ዕጩ መኮንን አዛዥ ኮሎኔል ከድር ጫጮ ተናግረዋል።
በመከላከያ ትምህርትና ስልጠና ዋና መምሪያ የሁርሶ አጭር ኮርስ ዕጩ መኮንን ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት ለመኮነንነት የሚያበቁ ስልጠናዎችን በመስጠት ብቁ ጀማሪ መኮንኖችን የማፍራቱን ጥረት አጠናክሮ መቀጠሉን የትምህርት ቤቱ አዛዥ ኮሎኔል ከድር ጫጮ ገልፀዋል ።
የአጭር ኮርስ ዕጩ መኮንን ትምህርት ቤት አዛዥ ኮሎኔል ከድር ጫጮ እንዳሉት ፣ የዕጩ መኮንኖችን የስልጠና ካሪኩለም አንዴ ብቻ ተቀርፆ የሚቀመጥ ባለመሆኑ ካሪኩለሙን በየጊዜው በማሻሻልና ጊዜውን የዋጀ ስልጠና መሥጠት እየተቻለ ነው።
ዕጩ መኮንኖቹ ስልጠናቸውን አጠናቀው ሲወጡ የሚመሩትን ሠራዊት ማሰልጠንና ለግዳጅ ለማዘጋጀት የሚያስችል እውቀት እንዲጨብጡ ይደረጋል ያሉት አዛዡ በየትኛውም ጊዜና ሁኔታ የሚሰጣቸውን ውስብስብ ግዳጅ ሁሉ በድል የሚፈፅሙበትን ወታደራዊ ችሎታም እንዲጎናፀፉ ይደረጋል ብለዋል።
የአጭር ኮርስ ዕጩ መኮንን ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት አዛዥ ኮሎኔል ከድር ሰልጣኞች በራሳቸው ጥረትና እውቀት የመሰብሰቢያ አደራሽ መገንባታቸውንም ገልፀዋል።
ሰልጣኞቹ የመማር ማስተማር ሂደቱ ምቹና የተሳለጠ እንዲሆን በግቢው ውስጥ እሳር ከመትከል ጀምሮ ግቢውን ውብ ፣ማራኪና አስደሳች ለማደረግ በፈጠራ የታገዙ የተለያዩ ስራዎችን እየሰሩ መሆናቸውን ተናግረዋል።
በበላቸው ክንዴ
ኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ቴሌግራም
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ