የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት መጋቢት 29 ቀን 2017 ዓ.ም
ስልጠና የመከላከያ ሠራዊቱን ሁለንተናዊ ብቃት በማሳደግ በኩል የሚጫወተው ሚና ከፍተኛ ነው ሲሉ የመከላከያ የሠው ሃብት አመራር ዋና መምሪያ ሃላፊ ሌተናል ጀኔራል አጫሉ ሸለመ ገለፁ።
የመከላከያ የሠው ሃብት አመራር ዋና መምሪያ ከሁሉም የመከላከያ ሠራዊት ክፍሎች የተወጣጡ የሠው ሃብት አመራር ባለሙያዎችን በሠው ሀብት አስተዳደር የሙያ ዘርፍ አሰልጥኖ አስመርቋል።
በሥልጠናው ማጠቃለያ ላይ የመከላከያ የሠው ሃብት አመራር ዋና መምሪያ ሃላፊ ሌተናል ጀኔራል አጫሉ ሸለመ የተገኙ ሲሆን በተካሔደው ስልጠና ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ ተመራቂዎች ሽልማት ከሰጡ በኋላ
ባደረጉት ንግግር መከላከያ እንደተቋም በሁሉም መስክ ስኬታማ የግዳጅ አፈጻጸም እያስመዘገበ እንደሚገኝ አውስተዋል።
በመከላከያ የሠው ሃብት አመራር ዋና መምሪያ በኩል በሠው ሀብት አስተዳደር የሙያ ዘርፍ ለወራት የተሠጠው ስልጠናም ወትሮ ዝግጁነትን ወደ ላቀ ምዕራፍ በማሸጋገር በኩል የሚያበረክተው አስተዋጽኦ ከፍተኛ መሆኑን ገልጸዋል።
ሌተናል ጀኔራል አጫሉ ሸለመ አክለው ተመራቂዎቹ በስልጠና ቆይታቸው የጨበጡትን እውቀት ወደ ተግባር በመቀየር የተቋሙን አሰራር እና ደንብ ማዕከል ባደረገ መልኩ ተልዕኳቸውን ሊወጡ ይገባል ብለዋል።
በኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርስቲ ቢዝነስ እና ማህበራዊ ጥናቶች ኮሌጅ ዳይሬክተር ኮሎኔል መላኩ ደመላሽ በበኩላቸው ሰልጣኞች በቆይታቸው የንድፈ ሀሳብ እና የተግባር ስልጠና በመከታተል የተመደበላቸውን የትምህርት ክፍለ ጊዜ በመሸፈን በሠው ሀብት አስተዳደር የሙያ ዘርፍ ትልቅ አቅም መጨበጣቸውን
ገልፀዋል
በስልጠና ቆይታቸው ሊያሰራቸው የሚችል በቂ ክህሎት ሊያዳብሩ መቻላቸውን ከተመራቂዎቹ መካከል አንዳንዶች በሰጡት አስተያየት ተናግረዋል።
ወንድማገኝ ታደሠ
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ቴሌግራም
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ