ያገለገሉ ተሽከርካሪዎችና ቁርጥራጭ ብረታ ብረቶች (ስክራፕ) በጨረታ ለመሸጥ የወጣ ማስታወቂያ
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ሚያዚያ 01 ቀን 2017 ዓ.ም
የሀገር መከላከያ ሚኒስቴር የሚገኙትን የተለያዩ ያገለገሉ ቀላልና ከባድ ተሸከርካሪዎችን ፣ የተለያዩ ቁርጥራጭ ብረታ ብረቶች (ስክራፕ) ፣ የአልሙኒየም ስክራፕ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈለጋል፡፡
1. ተጫራቾች የተዘጋጀውን የጨረታ ሠነድ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ ባሉት 5 ተከታታይ የስራ ቀናቶች ከጠዋቱ 2፡3o እስከ ıo፡00 ሰዓት ድረስ በአዲስ አበባ በሚገኘው መከላከያ ሠራዊት መኮንኖች ክበብ ግቢ ውስጥ ያገለገሉ ተሽከርካሪና የቁርጥራጭ ብረታ ብረት ሠነድ የማይመለስ ብር 1000.00 (አንድ ሺህ ብር ) ብቻ በመከፈል መግዛት ይኖርባቸዋል፡፡
2. ተጫራቾች ለእያንዳንዱ ተሽከርካሪና ለቁርጥራጭ
ብረታ ብረት (ስክራፕ) ለመሸጥ የተቀመጠውን ጠቅላላ ዋጋ 20 በመቶ (20%) /Ministry of Defense Property Sales Saving Account/ የሀገር መከላከያ ሚኒስቴር ንብረት ሽያጭ ማጠራቀሚያ ስም የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ተሞልቶ ከጨረታ ሠነዱ ጋር በማያያዝ በጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
3. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 የስራ ቀናቶች የሚሸጡ ተሽከርካሪዎችን ለማየት ኮፈን ተከፍቶ ስለሚቆይ ዘወትር በስራ ሠዓት ከጠዋቱ 2፡30 እስከ ıo፡00 ሠዓት ባለው ጊዜ ውስጥ ያገለገሉ ተሽከርካሪዎችን ደብረዘይት ( ቢሾፍቱ) በሚገኘው አውቶሞቲቭ ካምፕ ጀርባ ሲሆን ቁርጥራጭ ብረታብረቶች (ስክራፕ) በተመለከተ በደብረዘይት ( ቢሾፍቱ) ተሽከርካሪ ከምችት ግቢ፣በታንከኛና ብረት ለበስ ተሽከርካሪ ግቢ፣ በአዲስ አበባ ቃሊቲ በመልካ ገመኔ ትራንስፖርት ግቢ እና በጃልሜዳ መሐንዲስ ዋና መምሪያ ግቢ በስፍራው ተገኝተው መመልከት ይቻላል፡፡
4. ተጫራቾች ከጨረታ ሠነድ ጋር በተያያዘው የዋጋ ማቅረቢያ ቅፅ ብቻ ተጫራቾች የሚገዙበትን ዋጋ፣ ስማቸውን፣ክፍለከተማ፣ወረዳ፣የቤት ቁጥርና ስልክ ቁጥራቸውን በግልፅ በመፈረም ማቅረብ አለባቸው፡፡
5. ከጨረታው መዝጊያ ሰዓት በኋላ የሚደርሱ የጨረታ ሠነዶች ተቀባይነት የላቸውም፡፡
6. የጨረታው ሚያዚያ 16/2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 5፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚያው ቀን ከጠዋቱ 5፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በመከላከያ ሠራዊት መኮንኖች ክበብ ይከፈታል፡፡
7. አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፉበትን ገንዘብ አጠቃለው ከከፈሉ በኋላ ንብረቶቹን በ20 የስራ ቀናት ውስጥ የማንሳት ግዴታ አለባቸው፡፡
8. ለተሽከርካሪዎች የስም ማዞሪያ ወጭዎች እና ብረታ ብረቶቹን ለማንሳት የሚያስፈልግ ማንኛውም ወጭ ሙሉ በሙሉ በገዥዎች ይሸፈናል፡፡
9. ቁርጥራጭ ብረታ ብረቶችን ለመጫረት የሚፈልግ ተጫራች ከንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ብረታ ብረት የማቅለጥ ፈቃድ የተሠጠው ብቻ መሆን አለበቸው፡፡
10. መስሪያ ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ስበስጠ መረጃ፡- አድራሻ አዲስ አበባ ምድር ኃይል ግቢ መከላከያ ንብረት አስተዳደር ዳደሬክቶሬት ስልክ ቁጥር 0113-72-28-60 መደወል ይቻላል፡፡
የሀገር መከላከያ ሚኒስቴር
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ቴሌግራም