የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ሚያዚያ 06 ቀን 2017 ዓ.ም
የኮማንዶና አየር ወለድ ዕዝ አዛዥ ሌተናል ጄኔራል ሹማ አብደታ በመከላከያ ዋር ኮሌጅ ተገኝተው ለ3ኛ ባች መደበኛ ተማሪዎች የግንዛቤ ማስጨበጫ ትምህርት ሰጥተዋል። ጦርነት ካለው አሁናዊ የአለም ፖለቲካ ጋር ራሱን አያዘመነ ወቅቱን የሚጠይቅ ምላሽ የሚሰጥ ፈጣንና ተለዋዋጭ መልስ የሚሻ አውድ ነው ብለዋል።
ጄኔራል መኮንኑ ኢ-መደበኛ ጦርነት እና ፀረ-ሽምቅ ውጊያዎች ለማካሄድ አውዱን የተረዳ መቼና የት ሊከሰት ይችላል የሚል ስትራቴጂ መሪ ሲኖር ጦርነቱን በበላይነት ያጠናቅቃል ነው ያሉት።
አመራር ሁኔታውን በመረዳት በትንሽ ኪሳራ ትልቅ ድል ማስገንዘብ የሚችለው ራሱን በማብቃት በኘሮፌሽናል ሰራዊት ሲገነባ ነው ለዚህም ነው መከላከያ እንደ ተቋም የዘመናዊ ሠራዊት ስርዓተ ግንባታ ላይ በተቋም ደረጃ በትኩረት እየተሰራበት ያለ ብለዋል።
የመከላከያ ዋር ኮሌጅ ተማሪዎች ከሚማሩት የወታደራዊ ሳይንስ የንድፈ-ሃሳብ ጋር የሚዛመድ ካለው የሀገራችን ነባራዊ ሁኔታ ጋር አብሮ የተሰፋ መሆን አለበት ሲሉ በተግባር የተፈተነው ተሞክሯቸውን አስተላልፈዋል።
በአሰፉ ግርማይ
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ቴሌግራም
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official