ሠላምን በማፅናት ዕድገትና ብልፅግናን ለማረጋገጥ በቁርጠኝነት  እየተሰራ ነው። ዶክተር ጌድዮን ጢሞቲዎስ 

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ሚያዝያ 20 ቀን 2017 ዓ.ም

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስትር ክቡር ዶክተር ጌድዮን ጢሞቲዎስ በወቅታዊ ዓለም አቀፋዊ ፣ አህጉራዊ ፣ ቀጠናዊና  ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ለከፍተኛ የመከላከያ ሠራዊቱ አመራሮች ማብራሪያ ሰጥተዋል።

“የመሀሉ ዘመን” በሚል ርዕስ ትንታኔ ያቀረቡት ሚኒስትሩ በሀገራችን የመጣውን ለውጥ ተከትሎ በተመዘገቡ ሁለንተናዊ ድሎች ሳንዘናጋ ለበለጠ ድል መትጋት ይገባል ብለዋል።ታላቁን የህዳሴ ግድብ በከፍተኛ ፈተናዎች ውስጥ ገንብተን በማጠናቀቅ ሀገርና ህዝብን አንገት ከማስደፋት ለማዳን የተቻለበትና የጠላቶቻችን የተቀናጀ ሴራ ያከሸፍንበት አንዱ ማሳያ ነው ሲሉ ተናግረዋል።

ሀገራዊ ኢኮኖሚያችን ፈተናዎችን በመቋቋም በከፍተኛ ሁኔታ ማደጉንም ዓለም አቀፍና ሀገራዊ መረጃዎችን በማጣቀስ አብራርተዋል።

ባለፉት ዓመታት ብዙ ሀገራት በዲፕሎማሲው መስክ በትብብር ለመስራት ፍቃደኝነታቸውን ማሳየታቸውንና ይህንን በጎ ዕድል በመጠቀም የብሄራዊ ጥቅማችን ለማሳካት ጥረት እየተደረገ እንደሚገኝም ጠቁመዋል።

የሀገራችንን ብሄራዊ ጥቅም ለማረጋገጥና የባህር በር ተጠቃሚ ለመሆን ያቀረብነው ጥያቄ በዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ፍትሃዊ አጀንዳ ሆኖ መያዙንም ገልፀዋል።ተለዋዋጭና ኢ-ተገማች  በሆነው ዓለም አቀፋዊና ቀጠናዊ እንቅስቃሴ ያለንን ሁለንተናዊ ዝግጁነት በማረጋገጥና የተለያዩ ስልቶችን በመንደፍ  ተጋላጭነታችንን ለመቀነስ ስራዎች እየተሰሩ እንደሚገኝም ገልፀዋል።

በተከተልነው የሰላም ስምምነት የፀና  ወታደራዊ ድል ተመዝግቧል ያሉት  ዶክተር ጌድዮን ጢሞቲዎስ ፣ የሚያጋጥሙ ውስጣዊ ችግሮችን በሰላምና በይቅርታ በመፍታት በሀገርና በህዝብ ላይ የሚደርሰውን ጥፋት ለመቀነስ መንግስት እየወሰደው ያለው በሳል እርምጃ ከፍተኛ ውጤት ማስመዝገቡንም ተናግረዋል።

የሰላምን ጥሪ ባለመቀበል በሀይል ጥቅማችንን እናስከብራለን በማለት የሞከሩ የጥፋት ሀይሎች በተከተሉት የተሳሳተ ትርክትና ፖለቲካ ህዝቡ አንቅሮ እንደተፋቸውም ገልፀዋል።

የመከላከያ ሠራዊቱ ከሌሎች የፀጥታ ሀይሎች ጋር በመሆን በፅንፈኞች ላይ በወሰደው እርምጃም  ለሀገርና ለህዝብ ስጋት ከመሆን ወርደው የራሳቸውን ህልውና ለማቆየት እየተቸገሩ መምጣታቸውን አንስተዋል ።

ሠላምን ለማፅናትና ብልፅግናንን ለማረጋገጥ በቁርጠኝነት መስራት እንደሚገባ ገልፀው ጀግናው የመከላከያ ሠራዊታችንም ባስመዘገባቸው ድሎች ሳይኩራራ ለበለጠ ተልዕኮ ራሱን ማዘጋጀት ይገባዋል ብለዋል።

በውይይቱ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላን ጨምሮ ከፍተኛ የሠራዊቱ አመራሮች ተገኝተዋል።

በብዙአየሁ ተሾመ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ

https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 

https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ

https://www.facebook.com/fdredefense.official

ማስታወቂያ

No Posts Found

ክንውን

1
2
3
4
5
previous arrow
next arrow

ወቅታዊ አጀንዳ

IMG_20250620_160750_199
ኢትዮጵያና አሜሪካ በሠላምና በፀጥታ ጉዳይ በጋራ የመስራት ልምዳቸውን አጠናክረው ይቀጥላሉ።
IMG_20250620_202021_755
ኢትዮጵያ ለቀጠናው ሰላምና ደህንነት የምትወጣውን በጎ ሚና አጠናክራ እንደምትቀጥል ተገለፀ።
IMG_20250622_130413_910
ሠራዊቱ የታጠቀውን የዘመኑን ቴክኖሎጂ በወታደራዊ ኢንዱስትሪዎች በጥናትና ምርምር ማሳደግ ይገባል
IMG_20250615_181715_464
የኢፌዴሪ ጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለውጭ ግንኙነትና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ከሠጡት ማብራሪያ እና በምዕራብ ዕዝ ኮር ምሥረታ ላይ ካደረጉት ንግግር የተወሰደ፦
IMG_20250615_143244_103
ሠራዊቱ አስተማማኝ የሀገር ደጀንነቱን በተግባር እያረጋገጠ ይገኛል   ርዕሰ መስተዳድር አሻድሊ ሀሰን
IMG_20250615_125428_873
የመከላከያ ሠራዊት የታላቁ ሕዳሴ ግድብ እውን እንዲሆን ተልዕኮውን በብቃት እየተወጣ ነው

ስፖርት

IMG_20250620_160750_199
ኢትዮጵያና አሜሪካ በሠላምና በፀጥታ ጉዳይ በጋራ የመስራት ልምዳቸውን አጠናክረው ይቀጥላሉ።
IMG_20250620_202021_755
ኢትዮጵያ ለቀጠናው ሰላምና ደህንነት የምትወጣውን በጎ ሚና አጠናክራ እንደምትቀጥል ተገለፀ።
IMG_20250622_130413_910
ሠራዊቱ የታጠቀውን የዘመኑን ቴክኖሎጂ በወታደራዊ ኢንዱስትሪዎች በጥናትና ምርምር ማሳደግ ይገባል
IMG_20250615_181715_464
የኢፌዴሪ ጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለውጭ ግንኙነትና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ከሠጡት ማብራሪያ እና በምዕራብ ዕዝ ኮር ምሥረታ ላይ ካደረጉት ንግግር የተወሰደ፦
IMG_20250615_143244_103
ሠራዊቱ አስተማማኝ የሀገር ደጀንነቱን በተግባር እያረጋገጠ ይገኛል   ርዕሰ መስተዳድር አሻድሊ ሀሰን
IMG_20250615_125428_873
የመከላከያ ሠራዊት የታላቁ ሕዳሴ ግድብ እውን እንዲሆን ተልዕኮውን በብቃት እየተወጣ ነው

ኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት

ለህገ መንግስቱ፣ ለሀገራችን መንግስትና ህዝቦች ፍፁም ታማኝ የሆነ፣ ጦርነትን የሚያቆም የልህቀትና የፍቅር ማዕከል የሆነ፣ በአስተማማኝ እና በብቃት በአገር አቀፍና በአለም አቀፍ ግዳጅ የሚያሳካ ዘመናዊ የመከላከያ ሰራዊት ማየት።

ማህበራዊ ሚዲያ