ኢትዮጵያና ሞሮኮ በወታደራዊ ዘርፍ በትብብር  ለመስራት በሚያስችሏቸው ጉዳዮች ላይ ተወያዩ።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ሚያዚያ 19 ቀን 2017 ዓ.ም

የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ በሞሮኮ የሮያል ጦር ኃይል ኢንስፔክተር ጄኔራልና የደቡባዊ ዞን ጦር አዛዥ ሌተናል ጄኔራል መሐመድ ባሬድ የተመራ ልዑክን ተቀብለው አነጋግረዋል።

በ1955 ዓ.ም አካባቢ በይፋ የተጀመረው የኢትዮጵያና ሞሮኮ ታሪካዊ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት  በፓን አፍሪካዊ  መንፈስ እና ለአህጉራዊ አንድነት የጋራ ቁርጠኝነት የታየበት ወሳኝ ወቅት እንደነበር ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ አስታውሰዋል።

ባለፈው ዓመት በአዲስ አበባ እና በራባት የተካሄደው የከፍተኛ ደረጃ ወታደራዊ ልዑካን ምክክርም ሁለቱ ሀገሮች በትብብር ለመስራት የሚያስችሉ ጉዳዮችን እንዲፈትሹ እድል ፈጥሮላቸው እንደነበር ተገልጿል።

የሞሮኮ ሮያል ጦር ኃይል ኢንስፔክተር ጄኔራልና የደቡባዊ ዞን ጦር አዛዥ ሌተናል ጄነራል ሞሐመድ ባሬድ በበኩላቸው ለተደረገላቸው አቀባበል ምስጋና አቅርበው ኢትዮጵያ የአፍሪካ ነፃነት ምልክት መሆኗንና ወታደራዊ ትብብሩም ለአፍሪካ ሰላምና ደህንነት ለምናበረክተው አስተዋፅኦ የጎላ ሚና ይኖረዋል ብለዋል፡፡

ሁለቱ ሀገራት በተለያዩ የአፍሪካ ቀጠና የሚገኙ መሆናቸውን የገለፁት የመከላከያ ውጪ ግንኙነትና ወታደራዊ ትብብር ዋና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ሜጀር ጄነራል ተሾመ ገመቹ በየቀጠናቸው ከሚያበረክቱት አስተዋፅኦ በተጨማሪ በጋራ ለአፍሪካ ሰላምና ደህንነት እንዴት በትብብር መስራት እንዳለባቸውና ምን ምን ጉዳዮች ላይ መተባበር እንዳለባቸውም ውይይት ተደርጓል ብለዋል፡፡

ከሞሮኮ ወታደራዊ ተቋማት በቴክኖሎጂ ሽግግር በሳይበር በአየር ኃይልና በባህር ኃይል  ኢትዮጵያ የምትወስደው ተሞክሮ እንዳለ የገለፁት ጄነራል መኮንኑ  ኢትዮጵያ አሁን ላይ በኢንዱስትሪ እያሳየችው ካለው እምርታ አንፃር ደግሞ እነሱም አብረውን እንደሚሰሩና መጪውን ሁኔታ ያገናዘበ ልምድና ተሞክሮ በመለዋወጥ በቀጠናው በሚኖሩ የሰላምና ደህንነት ጉዳዮችም አብሮ ለመስራት የሚያስችል ውይይት መደረጉን ገልፀዋል፡፡

በውይይቱ ላይ የአየር ኃይል የባህር ኃይል የመከላከያ ትምህርትና ስልጠና እንዲሁም የሎጀስቲክስ ዋና መምሪያ ኃላፊዎች  ተገኝተዋል፡፡

ሁለቱ ሀገራት በቀጣይ የመግባቢያ ስምምነት ይፈራረማሉም ብለዋል፡፡ ውይይቱን ተከትሎ የልዑካን ቡድኑ በሆሚቾ አሙኔሽን ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪና በአየር ኃይል እየተከናወኑ ያሉ ተግባራትንም ጎብኝቷል፡፡

በአብዮት ዋሚ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ

https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 

https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ

https://www.facebook.com/fdredefense.official

ማስታወቂያ

No Posts Found

ክንውን

1
2
3
4
5
previous arrow
next arrow

ወቅታዊ አጀንዳ

s
ሠላምን በማፅናት ዕድገትና ብልፅግናን ለማረጋገጥ በቁርጠኝነት  እየተሰራ ነው። ዶክተር ጌድዮን ጢሞቲዎስ 
IMG_20250502_114207_631
ኢትዮጵያና ሞሮኮ በወታደራዊ ዘርፍ በትብብር  ለመስራት በሚያስችሏቸው ጉዳዮች ላይ ተወያዩ።
IMG_20250416_093208_823
የኢፌዴሪ ጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ክቡር ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ በሩዋንዳ የስራ ጉብኝት አደረጉ።
j,shuma
አመራር በትንሽ ኪሳራ ትልቅ ድል ማስመዝገብ የሚችለው ራሱን በማብቃት ዘመናዊ ሠራዊት ሲገነባ ነው። ሌተናል ጄኔራል ሹማ አብደታ
IMG_20250409_161558_051
የሚዲያ ስራችን በሠራዊታችን ተልዕኮና ግዝፈት ልክ መቃኘት ይኖርበታል።ሜጀር ጄኔራል እንዳልካቸው ወልደ ኪዳን
one
ስልጠና የመከላከያ ሠራዊቱን ሁለንተናዊ ብቃት በማሳደግ በኩል የሚጫወተው ሚና ከፍተኛ ነው  :-ሌተናል ጀኔራል አጫሉ ሸለመ

ስፖርት

ኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት

ለህገ መንግስቱ፣ ለሀገራችን መንግስትና ህዝቦች ፍፁም ታማኝ የሆነ፣ ጦርነትን የሚያቆም የልህቀትና የፍቅር ማዕከል የሆነ፣ በአስተማማኝ እና በብቃት በአገር አቀፍና በአለም አቀፍ ግዳጅ የሚያሳካ ዘመናዊ የመከላከያ ሰራዊት ማየት።

ማህበራዊ ሚዲያ