ኢትዮጵያ የሰላም ማስከበር ሚናዋን አዘምና ለመቀጠል ከመቼውም ጊዜ በላይ ቁርጠኛ መሆኗን የመከለካያ ሚኒስትሯ አስታወቁ።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ግንቦት 07 ቀን 2017 ዓ.ም

ኢትዮጵያ የሰላም ማስከበር ሚናዋን አዘምና ለመቀጠል ከመቼውም ጊዜ በላይ ቁርጠኛ መሆኗን የመከለካያ ሚኒስትሯ አስታውቀዋል። በሚኒስትሯ የሚመራው የልዑካን ቡድን በተመድ ሰላም ማስከበር የሚኒስትሮች ሰብሰባ ላይ በመካፈል ላይ ይገኛል።

በኢፌዴሪ የመከላከያ ሚኒስትር ክብርት ኢንጂነር አይሻ መሀመድ የተመራው የልዑካን ቡድን በጀርመን በርሊን እየተካሄደ ባለው የተባበሩት መንግስታት የሰላም ማስከበር የሚኒስትሮች ስብሰባ ላይ በመካፈል ላይ ይገኛል፡፡ ስብሰባው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት  የሰላም ማስከበር ተግባራትንና አፈፃፀሞችን፣ የአቅም ክፍተቶችና  በተልዕኮ ውጤታማነት ላይ ያተኮሩ ሪፎርምችን በተመለከተ ጥልቅ ውይይት የሚካሄድበት

ነው፡፡

በስብሰባው ላይ ንግግር ያደረጉት የመከላከያ ሚኒስትሯ ኢንጂነር አይሻ መሀመድ ኢትዮጵያ ለዓለም አቀፍ ሰላምና ደህንነት  ያላትን ዘመናትን የተሻገረ ቁርጠኝነት በማረጋገጥ በሰላም ማስከበር ስራዎች ተሳትፎዋን አዘምና እና አጠናክራ ለመቀጠል  ሁሌም ዝግጁ መሆኗን አስታውቀዋል፡፡ ሚኒስትሯ  አያይዘውም  በአሁኑ ወቅት  በዓለም አቀፍ የሰላም ማስከበር ተግባራት የፋይናንስ  ድጋፍ መቀነስ፣ የሰላም ማስከበር የአፈጻጸም ጥራት እና ታማኝነት መጓደል እንዲሁም ሰላም ማስከበር የሚካሄድባቸው አገራት እንደ ባለድርሻ አካላት ተሳትፏቸውን አለማጉላት ችግሮች አፅንኦት እንዲሰጣቸውም ጠይቀዋል፡፡

ኢትዮጵያዊያን በዓለም አቀፍ የሰላም ማስከበር ተልዕኮ  በዲሲፕሊን፣ በቁርጠኝነትና ሙያዊ ብቃታቸውን በማስመስከር ብሎም ከህዝብ ጋር ከፍተኛ ትስስር በመፍጠር ግዳጃቸውን በመፈጸም ረገድ አኩሪ ስም አትርፈዋል ያሉት ሚኒስትሯ አገራቸው የሰላም ማስከበር ተልዕኮን ከተቀላቀለችበት ጊዜ አንስቶ ቀዳሚ

አስተዋፅኦ  እያበረከተች ያለች መሆኗን ገልፀው ፤ በቀጣይም ይህንን ወደ ተሻለ ደረጃ  ለማሳደግ የሚያስችሉ ስራዎችን እየሰራች ትገኛለች  ብለዋል፡፡ በዓለም አቀፍ የሰላም ማስከበር ተልዕኮዎች ቁጥራቸው ቀላል የማይባል ሴት ሰላም አስከባሪዎችን በማሰማራቷና በውጤታማነቷም ኩራት ይሰማታል ሲሉም ገልፀዋል፡፡

ከዚሁ ጋር በተያያዘ ሚኒስትሯ በሰብሰባው ላይ እየተካፈሉ ከሚገኙት የእንግሊዝ ልዑካን ቡድን መሪ  እና parliamentary under-secretary of state for the armed  forces  ከሆኑት ሚስትር ሊክ ፖላርድ ጋር በጋራ ጉዳዮች ላይ መክረዋል፡፡

በሰብሰባው ኢትዮጵያን ጨምሮ ሌሎች የተመድ አባል አገራት በቀጣይ ለተመድ የሰላም ማስከበር ተልዕኮ ቃል እንደሚገቡ ይጠበቃል፡፡

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ

https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-

ማስታወቂያ

No Posts Found

ክንውን

1
2
3
4
5
previous arrow
next arrow

ወቅታዊ አጀንዳ

IMG_20250515_093603_746
ኢትዮጵያ የሰላም ማስከበር ሚናዋን አዘምና ለመቀጠል ከመቼውም ጊዜ በላይ ቁርጠኛ መሆኗን የመከለካያ ሚኒስትሯ አስታወቁ።
s
ሠላምን በማፅናት ዕድገትና ብልፅግናን ለማረጋገጥ በቁርጠኝነት  እየተሰራ ነው። ዶክተር ጌድዮን ጢሞቲዎስ 
IMG_20250502_114207_631
ኢትዮጵያና ሞሮኮ በወታደራዊ ዘርፍ በትብብር  ለመስራት በሚያስችሏቸው ጉዳዮች ላይ ተወያዩ።
IMG_20250416_093208_823
የኢፌዴሪ ጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ክቡር ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ በሩዋንዳ የስራ ጉብኝት አደረጉ።
j,shuma
አመራር በትንሽ ኪሳራ ትልቅ ድል ማስመዝገብ የሚችለው ራሱን በማብቃት ዘመናዊ ሠራዊት ሲገነባ ነው። ሌተናል ጄኔራል ሹማ አብደታ
IMG_20250409_161558_051
የሚዲያ ስራችን በሠራዊታችን ተልዕኮና ግዝፈት ልክ መቃኘት ይኖርበታል።ሜጀር ጄኔራል እንዳልካቸው ወልደ ኪዳን

ስፖርት

ኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት

ለህገ መንግስቱ፣ ለሀገራችን መንግስትና ህዝቦች ፍፁም ታማኝ የሆነ፣ ጦርነትን የሚያቆም የልህቀትና የፍቅር ማዕከል የሆነ፣ በአስተማማኝ እና በብቃት በአገር አቀፍና በአለም አቀፍ ግዳጅ የሚያሳካ ዘመናዊ የመከላከያ ሰራዊት ማየት።

ማህበራዊ ሚዲያ