የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ግንቦት 18 ቀን 2017 ዓ.ም
ጦርነትን ለማሸነፍ የስነ-ልቦና ዝግጁነት ወሳኝ ነው ሲሉ የመከላከያ ጤና ዋና መምሪያ ኃላፊ ሌተናል ጄኔራል ጥጋቡ ይልማ ተናገሩ።
ሌተናል ጄኔራል ጥጋቡ ይልማ በሰሜን ምዕራብ ዕዝ ማሰልጠኛ ማዕከል ተገኝተው በስልጠና ላይ ለሚገኙ የሬጅመንትና ሻምበል አመራሮች በሠራዊት የስነ-ልቦና ግንባታ ዙሪያ ትምህርት በሰጡበት ዕለት የተቋማችንን የፕሮፌሽናል ሠራዊት ግንባታ ስኬታማ ለማድረግ ደስተኛና በራሱ የሚተማመን፤ ስነ-ልቦናና አካላዊ ብቃቱ የተረጋገጠ ሁለንተናዊ አቅም ያለው አመራርና ሠራዊት ማዘጋጀት ወሳኝ ነው ብለዋል፡፡
ሌተናል ጄንራል ጥጋቡ ይልማ የሠራዊቱን ስነ-ልቦና ለማረጋገጥ በስልጠናና በዕውቀት ክህሎትን በማዳበር ከዘመኑ ጋር የሚዘመን በጠንካራ ስነ-ልቦና የምንመራው የጦር ክፍል ማሰልጠን፣መገንባትና ማብቃት ያስፈልጋል ሲሉ ተናግረዋል፡፡
የምንመራው ሠራዊት አቅሙ እንዲጎለበትና የሚሰጠውን ግዳጅ በድል እንዲወጣ አመራሩ ተከታታይነት ያለው የስነ-ልቦና ግንባታ ስራዎችን መስራት ይጠበቅበታል ብለዋል።
የመከላከያ ጤና ዋና መምሪያ ኃላፊ ሌተናል ጄኔራል ጥጋቡ ይልማ ፅንፈኛውን ኃይል በመደምሰስ በመስዋዕትነታችን ያረጋገጥነውን ሠላም የበለጠ ለማፅናት አቅማችንን ማጎልበትና ተልዕኳችንን በላቀ ብቃት ለመወጣት የበለጠ መዘጋጀት እንደሚገባም አሳስበዋል።
ዘጋቢ ይሁን አሻግሬ
ፎቶግራፍ እያሱ ጃርሶ
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ቴሌግራም
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official