የኢፌዲሪ መከላከያ ሠራዊት ግንቦት 28 ቀን 2017 ዓ.ም
የደቡብ ምዕራብ ሶማሊያ ከልል መንግስት የሴክተር 3 ዋና አዛዥ ሆነው ለቆዩት ብርጋዲየር ጀኔራል በስፋት ፈንቴ እና ለአዲሱ የሴክተር 3 ዋና አዛዥ ብርጋዲየር ጀኔራል ተክሉ ሁሬሳ የአሸኛኘትና የአቀባበል ሥነ-ስርዓት አካሂዷል፡፡
በዝግጅቱ ላይ የሃገር ሽማግሌዎችን በመወከል መላቅ መሃመድ ያቁብ ሼክ ዴሮው፣የክልሉን ሚኒስትሮች በመወከል የደቡብ ምዕራብ ሱማሊያ ኢንቨስትመንት እና ዕቅድ ሚኒስትር አቶ አብድሃኪም መሀመድ ሃጂ ፊቅ፣የባይድዋ ከተማ ከንቲባ አቶ አብዱላሂ ወቲን፣የባይ ዞን አስተዳደር አቶ አሊ ወርዴር ዶዮው የክልሉን መንግስት ወክለው ዕውቅናና ሽልማት አበርክተዋል።
ተወካዮቹ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ለሶማሊያ ህዝብ ለረጅም አመታት ውድ ህይወቱን የከፈለ አስካሁንም ድረስ ህዝባዊነቱ፣የግዳጅ አፈፃፀሙ በሶማሊያ ህዝብ የተመሰከረለትና በህዝብ ላይ ምንም ዓይነት ችግር እንዲደርስ የማይፈቅድ ቀጠናችንን ከመጠበቅና ሰላምን ከማረጋገጥ ባለፈ የተቸገሩትን በምግብ፣ በአልባሳት፣ በህክምናና በተለያዩ አገልግሎቶች ከኪስ ገንዘቡ በማዋጣት የሚረዳ የሚመሠገን ሠራዊት ነው ብለዋል፡፡
በዝግጅቱ ላይ የተገኙት የኤዩሶም ቺፍ ኦፍ ስታፍ ሜጀር ጀኔራል ክንዱ ገዙ የደቡብ ምዕራብ ሶማሊያ ህዝብና መንግስት ላዘጋጃችሁት ደማቅ አቀባበልና ሽኝት ስነ-ስርዓት በኢትዮጵያ መከላከያሠራዊትና ኤዩሶም ስም ምስጋና አቅርበዋል።
ለሠራዊታችንና ለሴክተሩ አመራሮች ያላችሁ ክብር ታላቅ እንደሆነ መረዳታቸውን የገለፁት ጄኔራል መኮንኑ ይህ ታላቅ ክብር ዛሬ የተጀመረ ሳይሆን የደቡብ ምዕራብ ሱማሊያ ህዝብና መንግስት ትላንት በአስቸጋሪ ወቅትም በአደባባይ ወጥቶ ኢትዮጵያዊያን የከፈሉትን ዋጋ እውቅና የሰጠን ህዝብና መንግስት ነው ብለዋል፡ቀጣይም ያለንን ግንኙነት አጠናክረን እንቀጥላለን ብለዋል፡፡
ዘጋቢ ሰመረ እሸቱ
ፎቶግራፍ አይናለም ተክለፃዲቅ
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ቴሌግራም
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ