ሌተናል ጀነራል ዘውዱ በላይ
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ግንቦት 30 ቀን 2017 ዓ.ም
የማዕከላዊ ዕዝ ጊቤ ኮር የማሰልጠን ተግባሩን አጠናክሮ በማስቀጠል ብቃት ያላቸው ተተኪ የበታች ሹም አመራሮች በኮሩ ጊዜያዊ ማሰልጠኛ በማሰልጠን አስመርቋል።
በሰልጣኞች የምርቃት መርሐ-ግብር በክር እንግድነት የተገኙት የማዕከላዊ ዕዝ ዋና አዛዥ ሌተናል ጀኔራል ዘውዱ በላይ ከዘመኑ የጦርነት ባህሪና የውጊያ አሰላለፍ የሚተጣጠፍና የመደበኛና የጉሬላ የውጊያ ስልት ፅንስ ሀሳብ አዳቅሎ በመተግበር ጠላቶቹን ድል በመንሳት የአገራችን ሰላም ማፅናት የሚችል ተተኪ አመራር በስልጠና በማብቃት ዝግጅነታችንን ማረጋገጥ የገባል ብለዋል።
የታሪካዊ ጠላቶቻችን አጀንዳ ተቀብለው የሰራዊታችን ስምና ጀግንነት ጥላሸት ለመቅባትና ስም ለማጥፋት የሚንቀሳቀሱ የማህበራዊ ሚድያ ቆማሪዎችና የሚያስተላልፉት መልዕክትና የሚያስተጋቡት ጩኸት የሰራዊት አመራሩና አባላት ልብ በማለት ግንዛቤ መውሰድ ይጠበቅበታል በማለት አፅንኦት ሰጥተዋል።
በመሀሪ ደበሳይ