የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ግንቦት 30 ቀን 2017 ዓ.ም
በምረቃው ላይ የሥልጠናውን ሪፖርት ያቀረቡት የኮሌጁ አዛዥ ብርጋዲየር ጀነራል ሙሉጌታ አምባቸው ፣ የተቋሙን ፍላጎት መሰረት በማድረግ ለመጀመሪያ ጊዜ በልዩ ሁኔታ የሰለጠኑት የክፍለ ጦር አመራሮች ውጤታማ በሆነ መልኩ ስልጠናቸውን አጠናቀው ለምረቃ መብቃታቸውን ገልፀዋል።
የሰራዊቱንና የአመራሩን አቅም ለመጨመር እየተደረገ ያለው ጥረት ማሳያ የሆነ ስልጠና መሰጠቱን የገለፁት አዛዡ ተግባራዊ ልምድ ላላቸው ከፍተኛ አመራሮቹ ተግባር ተኮር የሆነ ስልጠና መሰጠቱ ቀጣይ ለሚገጥማቸው ግዳጅ የሚኖራቸው ጠቀሜታ ከፍተኛ መሆኑን ተናግረዋል።
ስልጠናው በጊዜ በአቀራረብና በዓይነቱ ልዩ የነበረ የተቋሙን ፍላጎት ያሳካ መሆኑንም ገልፀዋል።
በምረቃው ላይ የመከላከያ ትምህርትና ስልጠና ሀላፊ ሌተናል ጀነራል ይመር መኮንንን ጨምሮ ከፍተኛ የሰራዊቱ አመራሮችና የኮሌጁ ማህበረሰብ ተገኝተዋል።
በብዙአየሁ ተሾመ