ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ሰኔ 04 ቀን 2017 ዓ.ም
በየብስም ሆነ በባሕር የሚቃጡ ትንኮሳዎችን የሚመክት ሠራዊት ተገንብቷል ሲሉ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ተናገሩ፡፡
በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የውጭ ግንኙነትና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የመከላከያ ሚኒስቴርን የ2017 በጀት ዓመት የ10 ወራት አቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ገምግሟል።
ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ በዚህ ወቅት እንዳሉት÷ መከላከያ ሠራዊቱ የምስራቅ አፍሪካ ቀጣናን ሰላምና ደህንነት በዘላቂነት ለማረጋገጥ በትኩረት እየሰራ ነው።
ኢትዮጵያ የባሕር በር እንድታገኝ ከቀጣናው ሀገራት ጋር በትብብር ለመስራትና በጋራ ለመበልጸግ ያላሳለሰ ጥረት እያደረገች እንደምትገኝ አንስተዋል፡፡
በአሁኑ ወቅት በየብስም ሆነ በባሕር የሚቃጡ ትንኮሳዎችን የሚመክት እንዲሁም የሀገሪቱን ሉዓላዊነት የሚያስከብር ሠራዊት መገንባቱን ነው ያስገነዘቡት፡፡
የመከላከያ ሚኒስትር ኢንጂነር አይሻ መሐመድ በበኩላቸው÷ የተቋሙን የማስፈጸም አቅም በማጎልበት ሀገርና ሕዝብን ከማንኛውም ጥቃት የመከላከል ሥራ በትኩረት እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡
ተዓማኒነት ያለው ነጻና ገለልተኛ ወታደራዊ የፍትህ ዳኝነት እየተሰጠ መሆኑን ጠቁመው ÷ የሠራዊቱን አስተማማኝ የሎጂስቲክስ ክምችት ማሟላት መቻሉንም ተናግረዋል፡፡
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ቴሌግራም
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ