ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ሰኔ 08 ቀን 2017 ዓ.ም
የመከላከያ ሠራዊት የኢትዮጵያዊያን ብሔራዊ ሃብት የሆነውን ታላቁ ሕዳሴ ግድብ እውን እንዲሆን ተልዕኮውን በብቃት እየተወጣ እንደሚገኝ የጦር ሃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ገለጹ።
ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የኢትዮጵያ ማንሰራራት በተግባር የታየበት መሆኑንም ገልጸዋል። የሕዳሴ ኮር ሦስተኛ ዓመት የምሥረታ በዓል ” ሕዳሴን በሕዳሴ ኮር ” በሚል መሪ ሐሳብ በታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ እየተከበረ ይገኛል።
በበዓሉ አከባበር ላይ የቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አሻድሊ ሀሰን፣ የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ስራ አስኪያጅ ኢንጅነር ክፍሌ ሆሮ፣ የምዕራብ ዕዝ ዋና አዛዥ ሌተናል ጄኔራል መሠለ መሰረት፣ ጄኔራል መኮንኖች፣የክልሉ ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ሃላፊዎች ታድመዋል።
የጦር ሃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ እንደገለጹት፥ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የኢትዮጵያውያን ብሔራዊ ሃብት ነው።
መከላከያ ሠራዊት ለግድቡ ሁሉን አቀፍ ስኬት የበኩሉን መወጣቱን ገልጸው፤ የታላቁን ሕዳሴ ግድብ ደህንነትን ከማስጠበቅ አኳያም ታላቅ አርዓያነት ማከናወኑን ተናግረዋል።
የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ዛሬ የደረሰበት ደረጃ እንዲደርስም ተልዕኮውን በብቃት መፈጸሙን ጠቅሰዋል። ሠራዊቱ የኢትዮጵያዊያን ብሔራዊ ሃብት የሆነውን የታላቁ ሕዳሴ ግድብ እውን እንዲሆን በጀግንነት ደህንነቱን በማስጠበቅ ተልዕኮውን መፈጸሙን ገልጸዋል።
ሠራዊቱ ኢትዮጵያ እንድትሻገር የሚያበረክተውን ሁሉን አቀፍ ተግባር አጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል። ዘገባው የኢዜአ ነው
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ቴሌግራም
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ