የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ሰኔ 08 ቀን 2017 ዓ.ም
👉 በየትኛውም ሁኔታ የሚቃጡ ትንኮሳዎችን የሚመክት ሠራዊት ተገንብቷል፤
👉 መከላከያ ሠራዊቱ የምስራቅ አፍሪካ ቀጠናን ሰላምና ደህንነት በዘላቂነት ለማረጋገጥ በትኩረት እየሰራ ነው፤
👉 ኢትዮጵያ የባሕር በር እንድታገኝ ከቀጠናው ሀገራት ጋር በትብብር ለመስራትና በጋራ ለመበልጸግ ያላሳለሰ ጥረት እያደረገች ነው፤
👉 በየብስም ሆነ በባሕር የሚቃጡ ትንኮሳዎችን የሚመክት እንዲሁም የሀገሪቱን ሉዓላዊነት የሚያስከብር ሠራዊት ተገንብቷል፤
👉 ምስራቅ አፍሪካ በየብስም በባህርም ችግር ያለበት ቀጠና ነው ችግሩን በጋራ ለመፍታት ዝግጁ ነን ነገር ግን ኢትዮጵያ ወደ ባህር በር እንዳትጠጋ የሚፈልጉ ሀይሎች አሉ፤
👉 ሁሉም የኢትዮጵያ ግዛት የመከላከያ ሠራዊቱ ግዛቱም መኖሪያውም ነው፤
👉 ያልደረስንበት ትላልቅ የቴክኖሎጂ ጉዳይ ካልሆነ በስተቀር ክላሽና የመድፍ ጥይት ለመግዛት ገበያ አንወጣም፤
👉 በሶማሊያ አልሸባብ ገብተው የገደልናቸው ኢትዮጵያዊያን አሉ ፣በሱዳን የእርስ በእርስ ግጭት ለአንዱ ወገን ወግኖ የተዋጋ አለ አሁን ደግሞ የሻዕቢያ ቅጥረኛ ለመሆን የተዘጋጀ ኢትዮጵያዊ አለ፤
👉 የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት መኮንንም ሆነ አባል ኦቨር ታይም /ትርፍ ሰዓት/ሥለሠራሁ ይከፈለኝ አይልም፤
👉 በከፍተኛ ደረጃ ጠላትን አዳክመናል ክልሎች የራሳቸውን ሃይል እያጠናከሩ ውስጣቸውን እያጠሩ ራሳቸውን እየቻሉ ነው፤
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ቴሌግራም
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ