የቀድሞ የ20ኛ ሜካናይዝድ ክፍለ ጦር ስፖርተኞች እና የሠራዊት አባላት 80ኛ ዓመት መቻል ለ ኢትዮጵያ የጎዳና ሩጫ ላይ እንደሚሳተፉ አሥታወቁ።
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ሰኔ 17 ቀን 2016 ዓ.ም
የቀድሞ 20ኛ ሜካናይዝድ ስፖርተኞች እና የሠራዊት አባላት መቻል ለኢትዮጵያ ሰኔ 23 ቀን 2016 ዓ.ም መነሻ እና መዳረሻውን መስቀል አደባባይ ለሚያደርገው የጎዳና ላይ ሩጫ ለመሳተፍ የመሮጫ ማሊያ ግዥ ፈፅመዋል።
መቻል የኛ ነው እኛም የመቻል ነን ያሉት የቀድሞ የ20ኛ ሜካናይዝድ ክፍለ ጦር አባላት እና ስፖርተኞች ማህበር ሰብሳቢ ሻምበል መገርሳ ሁንዴ የጎዳና ላይ ሩጫው እንድንሳተፍ በመጋበዛችን ትልቅ እድል ነውና በጣም ደስተኞች ነን ብለዋል።
መቻልን መደገፍ ሠራዊቱን መደገፍ መሆኑን የገለፁት የማህበሩ መስራች እና ምክትል ሰብሳቢ ምክትል አስር አለቃ ገብረሚካኤል ጫላ በዚህ ታሪካዊ ክብረ በዓል ላይ መሳተፍ በመቻላችን ዕድለኞች ነን ብለዋል።
ዘጋቢ ገረመው ጨሬ
ፎቶግራፍ ገረመው ጨሬ
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ቴሌግራም
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ