ዋና ዳይሬክቶሬቱ ሠራዊቱንና ቤተሠቡን በፍትሃዊነት እያገለገለ ነው።   ሜጄር ጄኔራል አብዱ ከድር

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ሰኔ 03 ቀን 2017 ዓ.ም

በጠቅላይ መምሪያው የጠቅላላ አገልግሎት ዋና ዳይሬክቶሬት በተሠጠው ዝርዝር ሃላፊነቶች መሠረት ሠራዊቱንና ቤተሠቡን በፍትሃዊነት እያገለገለ እንደሚገኝ የዋና ዳይሬክቶሬቱ ዳይሬክተር ሜጄር ጄኔራል አብዱ ከድር ገለፁ።

አሠራርና መመሪያው በሚያዘው መሠረት የሠራዊቱን የመኖሪያ ቤትና የሥራ መገልገያ ቢሮዎችን ማመቻቸት ፣እንደ ውሃ መብራትና ሌሎች አገልግሎት መሥጫዎችን መከታተል እንደአሥፈላጊነቱ የመጠገንና ለአገልግሎት ምቹ የማድረግ ሥራዎች በክፍሉ እየተከናወነ ሥለመሆኑ አሥረድተዋል።

የካምፖችና ቤቶች አሥተዳደር ከቤት ዕደላና ከጥገና ሥራዎች ጋር በተያያዘ አሥፈላጊውን ክትትል እያደረገ ሥለመሆኑ የተናገሩት ሜጄር ጄኔራል አብዱ ከድር እየተጠናቀቀ ባለው የ2017 በጀት ዓመት ከአንድ ሺህ በላይ ቤቶች ለሠራዊት መታደላቸውንና የመኖሪያ ቤት እጥረትን ሊቀርፉ የሚችሉ በርካታ ቤቶች በካምፖች በተለይም ደግሞ በጎፋ ካምፕ እየተገነቡ መሆኑን ተናግረዋል።

ሠራዊቱንና ቤተሠቡን ከመደጎም አንፃር በመደብሮችና መዝናኛ ክበቦች አማካኝነት በርካታ ችግር ፈች ተግባራት እየተከናወኑ መሆኑንም ገልፀዋል። በአነስተኛና ተመጣጣኝ በሆነ ዋጋ እንደ ዘይት ስኳር ፊኖ እና መሠል የሸቀጣሸቀጥ ፍጆታዎች ለሠራዊቱ ተደራሽ እንደሚሆኑና ክበቦች በአነስተኛ ዋጋ ለሠራዊቱ አሥፈላጊውን የምግብ አገልግሎት እንደሚሠጡም አንስተዋል።

የወተት ላሞች በማርባት በየካምፑ ለሠራዊቱ የወተት አቅርቦት ማከናወን፣ በጠቅላይ መምሪያው በሚገኘው ሀይቅ ዓሣ በማሥገር ለሠራዊቱ ክፍሎች ማድረስ፣ የዶሮ እርባታ በሠፊው መሣተፍ ፣እንቁላል ለተጠቃሚው ማድረስ እና መሠል ሥራዎች ላይ ትኩረት በማድረግ የሠራዊቱንና ቤተሠቡን ኑሮ መደጎም እየተቻለ መሆኑን እና ቀጣይ ይበልጥ ሥራው ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ሜጄር ጄኔራል አብዱ ከድር አረጋግጠዋል።

ዘጋቢ ውብሸት ቸኮል

ፎቶግራፍ ደጀኔ አሳይቶ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ

http://localhost/defensenew

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ

https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 

https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ

https://www.facebook.com/fdredefense.official

ወቅታዊ አጀንዳ

33
ኮሌጆች እና ማሰልጠኛ ትምህርት ቤቶች የተቋሙን ዝግጁነት የሚያጠናክር ውጤታማ ስራዎችን ሠርተዋል።
32
ተቋሙን የሚመጥን ሎጀስቲክሳዊ ስራ ከምንጊዜውም በላይ እየተሠራ ነው፡፡ሌተናል ጀኔራል አብዱራህማን እስማኤል
31
ቆራጥና ግዳጁን በጀግነት የሚፈፅም መሪና ሠራዊት ማፍራት ተችሏል።     ሌተናል ጀኔራል ሰለሞን ኢተፋ
30
የውጭ ጠላቶቻችን ኢትዮጵያን አቅም የሌላትና ደካማ ሀገር ለማድረግ ከመስራት አይቆጠቡም   ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ
29
የልዩ ዘመቻዎች ዕዝ የሚጠበቅበትን ተልዕኮ በውጤት እየፈፀመ መሆኑ ተገለፀ።
28
ዕዙ የተሰጠውን ሀገራዊ ተልዕኮ ከምንጊዜውም በላይ በውጤታማነት እየተወጣ ይገኛል።     ሌተናል ጄኔራል መሰለ መሰረት

ስፖርት

ኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት

ለህገ መንግስቱ፣ ለሀገራችን መንግስትና ህዝቦች ፍፁም ታማኝ የሆነ፣ ጦርነትን የሚያቆም የልህቀትና የፍቅር ማዕከል የሆነ፣ በአስተማማኝ እና በብቃት በአገር አቀፍና በአለም አቀፍ ግዳጅ የሚያሳካ ዘመናዊ የመከላከያ ሰራዊት ማየት።

ማህበራዊ ሚዲያ