የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ሃምሌ 19 ቀን 2017 ዓ.ም
የምዕራብ ዕዝ ከፍተኛ አመራሮች በዕዙ ጠቅላይ መምሪያ የበጀት ዓመቱን እቅድ አፈፃፀም ዙሪያ ውይይት አድርገዋል።
በውይይቱ ማጠቃልያ ላይ የተገኙት የምዕራብ ዕዝ ዋና አዛዥ ሌተናል ጄኔራል መሰለ መሰረት የውስጥም ሆነ የውጭ ፀረ-ሰላም ሃይሎችን በመደምሰስ አንፀባራቂ ድል ከማስመዝገብ የሚያግደን ሃይል አለመኖሩን በተግባር እያረጋገጥን እንገኛለን ብለዋል።
ሠራዊቱ እንደባለፉት ጊዜያቶች ሁሉ የተሰጠውን ትልቅ ሃገራዊ ግዳጅ ውጤታማ በሆነ መልኩ እየፈፀመ የሚገኝ መሆኑን ገልፀው ለተልዕኮው ቅድሚያ ሰጥቶ በመስራት የበለጠ ድል ማስመዝገብ የሚያስችለው የዝግጁነት ደረጃ ላይ እንደሚገኝም ገልፀዋል።
ሠራዊታችን በተሰማራበት ቀጠና በሽብርተኝነት ተግባር ላይ ተሰማርተው የሃገራችን የሰላም ማነቆ እየሆኑ ያሉ ፅንፈኛ ሃይሎችን ዳግም የህዝባችን ስጋት እንዳይሆኑ ለማድረግ የማያዳግም እርምጃ እየወሰደ መሆኑንም ጄኔራል መኮንኑ ተናግረዋል፡፡
ሌተናል ጄኔራል መሰለ መሠረት በቀጠናው የፅንፈኛውን እና የአሸባሪውን የሸኔ ቡድን በመደምሰስ ያሳካናቸውን ድሎች አቅበን የህዝባችንን ሰላም ዘላቂነት ለማረጋገጥ መስራትና ከአካባቢው የመስተዳደር አካላት ፣ የፀጥታ ሃይሎች ፣ ከሃገር ሽማግሌዎችና የሃይማኖት አባቶች ጋር በመቀናጀት ዘላቂ ሰላም ማረጋገጥና ዋስትና ሆኖ መቀጠላችን ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።
ዕዙ ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ መሰረተ ድንጋይ ከተቀመጠበት ዕለት ጀምሮ እስከ ፍፃሜው ዋዜማ ድረስ ያለምንም የፀጥታ ችግር እንዲከናወን መደረጉ የሠራዊታችንን ጥንካሬ ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ ነው ሲሉ ተናግረዋል።
ከህዝባችን ጋር ያለንን የሰላም እና የልማት ትስስር ይበልጥ አጠናክረን በመቀጠል የኢትዮጵያን ሰላም እና አንድነት አስጠብቀን ማቆየት አለብንም ብለዋል።
ዘጋቢ ፍፁም ከተማ
ፎቶ ግራፍ ሽመልስ እሸቱ
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
http://localhost/defensenew/
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
http://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ቴሌግራም
http://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
http://www.facebook.com/fdredefense.official
