የኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርሲቲ በሀገራችን ሞዴል የሆነ ዩኒቨርሲቲ ነው   ክቡር ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ሰኔ 17 ቀን 2017 ዓ.ም

የኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርሲቲ የወታደራዊ ቴክኖሎጅ አቅምን በማሳደግ ረገድ ጠንካራ የምርምርና የልማት ሥራዎችን እያከናወነ ይገኛል።

ዩኒቨርሲቲው የሠራዊታችንን ወታደራዊ የቴክኖሎጅ አቅም በማሣደግም ሆነ የልማትና ምርምር ማዕከል በመሆን በርካታ በራስ አቅም የተሠሩ ሥራዎችን እያከናወነ ነው። ዛሬ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላና ከፍተኛ የሠራዊቱ አመራሮች ይህንኑ ሥራ ተመልክተዋል።

ዩኒቨርሲቲው ሳይንሳዊ በሆነ አግባብ እየሰራቸው የሚገኙ ተሰፋ ሰጪ የምርምርና የልማት ተግባራት በቀጣይነት የመከላከያን ወታደራዊ አቅም የበለጠ ማሳደግ የሚችሉ ዩኒቨርሲቲዉ በሀገራችን በዚሁ ዘርፍ ሞዴል መሆኑን የሚያረጋግጡ የከፍታ ማሳያ ሥራዎች መሆናቸውን ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ አረጋግጠዋል።

ዘመኑ የቴክኖሎጂ እሽቅድድም የሚሥተዋልበት እንደመሆኑ መጠን ኢትዮጵያ ከዘመኑ ቴክኖሎጂ ጋር ራሷን ማላመድ የምትችልበትን ጥበብ መፍጠር እንደሚገባ ያመላከቱት ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ በዩኒቨርሲቲው የታዩ የተጀመሩ የምርምርና የልማት ሥራዎችን ለማሣደግ ተቋሙ አሥፈላጊውን ድጋፍ ሁሉ ያደርጋል ብለዋል።

በሠው ሃይል ግንባታ በኩል ሀገሩን የሚወድ የሠለጠነ ዩኒቨርሲቲውን የሚወክል ሀይል መፍጠር ላይ ትኩረት ማድረግ እንደሚገባ የጠቆሙት የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ ለተቋሙ የከፍታ ጉዞ ለሚተጉ ለዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ብርጋዲየር ጄኔራል ከበደ ረጋሳና ለዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ አመሥግነዋል።

በመማር ማሥተማር ሂደቱ ከፍተኛ ደረጃ ላይ የደረሠውና በማህበረሰብ አቀፍ አገልግሎት ስራው በርካታ ተግባራትን እያከናወነ የሚገኘው የኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርሲቲ አሥራ ሦስት የምርምርና ልማት ሥራዎችን ሥለማጠናቀቁና አሥራ አንዱ ደግሞ በሥራ ሂደት ላይ ሥለመሆናቸው ተገልጿል።

ዘጋቢ ውብሸት ቸኮል

ፎቶግራፍ ተሰማ ኡርጌሳ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ

http://localhost/defensenew

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ

https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 

https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ

https://www.facebook.com/fdredefense.official

ወቅታዊ አጀንዳ

33
ኮሌጆች እና ማሰልጠኛ ትምህርት ቤቶች የተቋሙን ዝግጁነት የሚያጠናክር ውጤታማ ስራዎችን ሠርተዋል።
32
ተቋሙን የሚመጥን ሎጀስቲክሳዊ ስራ ከምንጊዜውም በላይ እየተሠራ ነው፡፡ሌተናል ጀኔራል አብዱራህማን እስማኤል
31
ቆራጥና ግዳጁን በጀግነት የሚፈፅም መሪና ሠራዊት ማፍራት ተችሏል።     ሌተናል ጀኔራል ሰለሞን ኢተፋ
30
የውጭ ጠላቶቻችን ኢትዮጵያን አቅም የሌላትና ደካማ ሀገር ለማድረግ ከመስራት አይቆጠቡም   ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ
29
የልዩ ዘመቻዎች ዕዝ የሚጠበቅበትን ተልዕኮ በውጤት እየፈፀመ መሆኑ ተገለፀ።
28
ዕዙ የተሰጠውን ሀገራዊ ተልዕኮ ከምንጊዜውም በላይ በውጤታማነት እየተወጣ ይገኛል።     ሌተናል ጄኔራል መሰለ መሰረት

ስፖርት

ኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት

ለህገ መንግስቱ፣ ለሀገራችን መንግስትና ህዝቦች ፍፁም ታማኝ የሆነ፣ ጦርነትን የሚያቆም የልህቀትና የፍቅር ማዕከል የሆነ፣ በአስተማማኝ እና በብቃት በአገር አቀፍና በአለም አቀፍ ግዳጅ የሚያሳካ ዘመናዊ የመከላከያ ሰራዊት ማየት።

ማህበራዊ ሚዲያ