የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ክቡር ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ከሲቲሳምቪኤም (CTSAMVM) ተወካዮች ጋር ተወያይተዋል።
የሲቲሳምቪኤም ተወካይ ልዑካን ቡድን አባላት ኢትዮጵያ ለደቡብ ሱዳን ለምታደርገው ያልተቋረጠ ድጋፍ ያላቸውን አድናቆት በመግለፅ ፤ በደቡብ ሱዳን እንዲሁም የቀጠናውን ሠላም ለማጠናከር እና ዘላቂ ሠላምን ለማረጋገጥ እያጋጠሙ ያሉ ተግዳሮቶችን በቁርጠኝነት ለመወጣት እንዲችል ከኢትዮጵያና ከሌሎች አባል ሀገሮች ጋር በጋራ እየሰሩ ያሉትን ሥራ አጠናክረው ለመቀጠል ቁርጠኛ መሆናቸውን ተናግረዋል።
ኢትዮጵያ የምታደርገው ድጋፍ እና ክትትል እንደማይለያቸው ያላቸውን ፅኑ ዕምነትም ገልፀዋል።
የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ክቡር ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ሲቲሳምቪኤም (CTSAMVM) እያደረገው ያለውን ሥራ በማድነቅ ለደቡብ ሱዳን ህዝብና መንግሥት እንዲሁም ለቀጠናው ሰላምና መረጋጋት ኢትዮጵያ የበኩሏን አስተዎጽኦ ማበርከቷን አጠናክራ እንደምትቀጥል አረጋግጠዋል። መረጃውን ያደረሠን የመከላከያ ህዝብ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት ነው