የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት የካቲት 07 ቀን 2016 ዓ.ም
መብረቅ ክፍለ ጦር ሰሞኑን ባደረገው ዘመቻ የአሸባሪው ሸኔ አመራሮችና አባላት ሲመቱ መገናኛ ሬዲዮን ጨምሮ በርካታ የጦር መሳሪያ እና ተተኳሽች በቁጥጥር ስር ውለዋል።
በቄለም ወለጋ ዞን ጊዳሚ ወረዳ ቄለም ፣ ግራይ ሶንካና አቦቴ አካባቢ የሸኔ ሽብር ቡድን ላይ በተሰነዘረ ማጥቃት ጃል አብዲ፣ ጃል ጉርሜሳ፣ ጃል በዳሳ ተስፋዬና ጃል ገመቹ የተባሉ አራት ዋና ዋና አመራሮቹ ተገድለዋል።
የመብረቅ ክፍለጦር ምክትል አዛዥ ለውጊያ ድጋፍ አገልግሎት ሌተናል ኮሎኔል ንጉሴ ጥላሁን እንዳሉት፦
ከአመራሮቹ መደምሰስ ባለፈ በርካታ አባላቱ ሙት ሆነው በአካባቢው ይንቀሳቀስ የነበረው የሽብር ቡድኑ የመገናኛ ሬድዮ፣መሳሪያና ተተኳሽ በመማረክ አቅሙን ማንኮታኮት ተችሏል።
ምክትል አዛዡ ጨምረው እንዳስረዱት ከመሳሪያና ተተኳሾች ባለፈ የተለያዩ ቁሳቁሶች የተማረኩበት ሲሆን በዚህኛው ዘመቻ በርካታ ሃይል ለማሰለፍ የሞከረው ሸኔ ከፍተኛ ምት ደርሶበታል።
ለሽብር ቡድኑ መደምሰስ የአካባቢው ማህበረሰብ ከክፍለ ጦሩ ጋር በቅንጅት መስራቱ ከፍተኛ ሚና እንደነበረው የክፍለጦሩ አመራሮች በአስተያየታቸው የገለጹት።
ዘጋቢ ዮሴፍ ጉርቢያው
ፎቶግራፍ ዮሴፍ ጉርቢያው