በዚሁ የምረቃ ስነ-ሥርዓት ላይ በክብር እንግድነት የተገኙት የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ክቡር ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ፣ ቀደምት አርበኞች ያለጫማ፣ ባልሰለጠነ የሰው ሀይል እና ባልሰለጠነ መሣሪያ የሀገር ውስጥና የውጭ ጠላትን መክተው ሀገር በደማቸውና በአጥንታቸው ማግረው አስረክበውናል፤ እናንተም የእለቱ ተመራቂዎች የቀደምት አርበኞች ልጆች እንደመሆናችሁ መጠን ሀገርን ጠብቃችሁ ለትውልድ ማስረከብ ይኖርባችኋል ብለዋል።

የኮርሱ ስያሜ ንስር እንደመሆኑ የበራሪዋን የንስርን ጠላትን ከሩቅ የመመልከት፣ ከፍ ብሎ የመብረርን እና ከሀይል በላይ የሆነ ጠላት ሲገጥም ከሩቅ ተመልክቶ የመደምሰስን እንዲሁም ራስን በስልጠና በየጊዜው መለወጥን እንደንስሯ በራሪ አህዋፍ ባህሪ ልትላበሱ ይገባል ሲሉ አሥገንዝበዋል።
ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ ሀገራችን ከጥንትም ጀምሮ ከውስጥም ይሁን ከውጭ ጠላት የማታጣ በመሆኗ አሁንም ሀገርን ለማዳከም የውጭ አጀንዳ ተቀብለው የሚገኙ ፀረ ሰላም ሀይሎች ለማተራመስ ጥረት እያደረጉ የሚገኙ ቢሆንም ኢትዮጵያ ሰላሟ የተረጋገጠ ያደገችና የበለፀገች ሆና ልጆቿን ማኖር እንድትችል በስልጠና ያገኛችሁትን አቅም መጠቀም ይኖርባችኋል ሲሉ አሳስበዋል።

በእለቱ በስልጠናው ብልጫ ላመጡ ተመራቂዎችና ለስልጠናው መሳካት ድጋፍ ላደረጉ አካላት እውቅናና ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።
በዚሁ የዕጩ መኮንኖች የምረቃ መርሃ ግብር ላይ ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላን ጨምሮ ጀኔራል ጌታቸው ጉዲና፣ የመከላከያ ትምህርት እና ስልጠና ዋና መምሪያ ኃላፊ ጀኔራል ይመር መኮንን፣ የድሬደዋ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀር፣ጀነራል መኮንኖች፣ የሠራዊት አባላት፣ አባ ገዳዎችና የአካባቢው ማህበረሰብ ተገኝተዋል።

ዘጋቢ ልደት አስረስ
ፎቶ ግራፍ አበረ አየነው