ዛሬ ኢትዮጵያ የሾመቻችሁ የመከላከያ የጦር መኮንኖች እንኳን ደስ አላችሁ።
ውትድርና በመሥዋዕትነት ላይ የተመሠረተ አገልግሎት ነው። ከሕይወት የበለጠ ክብር የለምና ሕይወት ከመስጠት የበለጠ ስጦታ የለም።
ዛሬ የተቀበላችሁት ሹመት የሠራዊቱን ቀጣይነት ያለው ግንባታ፣ የኢትዮጵያን ማኅፀነ ለምለምነት፣ የእናንተንም ትጋት ያሳያል።
በቀጣዩ አገልግሎታችሁ ሠራዊታችንን የበለጠ በማዘመን በአቋምና በዓቅም የላቀ እንደምታደርጉ አምናለሁ።