የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት የካቲት 03 ቀን 2016 ዓ.ም
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ሃላፊዎች በተገኙበት የዓድዋ ድል መታሰቢያ የምረቃ ሥነ-ሥርዓት እየተካሄደ ነው።
በምረቃ ሥነ-ሥርዓቱም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር)፣ ፕሬዚዳንት ሳኅለወርቅ ዘውዴ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ የጦር ሃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ እንዲሁም የሁለቱ ምክር ቤቶች አፈ-ጉባዔዎችን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግሥት ሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶር) እና ፕሬዚዳንት ሳኅለወርቅ ከዓድዋ ድል መታሰቢያው ሥር የአበባ ጉንጉን አስቀምጠዋል፡፡